ድምፃዊ ሳሚ ዳን ለፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው አርሰናል አዲስ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ሊለቅ ነዉድምፃዊ ሳሚ ዳን ለፕሪሚየር ሊግ ዋን…

- Advertisement -
Sidebar AD
ድምፃዊ ሳሚ ዳን ለፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው አርሰናል አዲስ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ሊለቅ ነዉ
ድምፃዊ ሳሚ ዳን ለፕሪሚየር ሊግ ዋንጫው ባለቤት አርሰናል አዲስ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ሊለቅ መሆኑን አስታወቀ።
ድምፃዊ ሳሚ ዳን መድፈኞቹ ከ22 ዓመታት ረጅም የጥበቃ ጊዜ በኋላ የኢንግሊሽ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማንሳታቸውን ተከትሎ፣ ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ አዲስ ልዩ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ለአድማጮች እንደሚያደርስ ይፋ አድርጓል።
ታዋቂው ድምፃዊ ለአርሰናል ክለብ ያለውን ጥልቅ ፍቅርና አጋርነት በገለጸበት ማስታወቂያው፥ My አርሴ እማ አንድ ሙዚቃማ ይገባታል!!! 12 ሰዓት 🙌”በማለት የስሜቱን መጋፈል የገለጸ ሲሆን፣ ሙዚቃው ክለቡና ደጋፊዎቹ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያሳለፉትን ውጣ ውረድና አሁን የተቀዳጁትን ታላቅ ድል የሚያጣጥም እንደሚሆን ይጠበቃል።
የአርሰናልን የዋንጫ ድል ተከትሎ በርካታ ታዋቂ ሰዎችና ከያንያን ደስታቸውን እየገለጹ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ በሳሚ ዳን የሚለቀቀው አዲስ ዜማ በማህበራዊ ሚዲያ እና በስፖርት አፍቃሪው ዘንድ ከፍተኛ ጉጉትን ፈጥሯል።Via ጉርሻ page
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1