⚡️ በኢራን እና አሜሪካ መካከል አዲስ የሰላም ማሻሻያ ሃሳቦች በፓኪስታን በኩል መለዋወጣቸው ተገለጸ!
የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ኢራን ከሶስት ቀናት በፊት በፓኪስታን አምባሳደር በኩል 14 ነጥቦችን የያዘ አዲስ የተሻሻለ የሰላም ረቂቅ ሰነድ ለአሜሪካ ካስገባች በኋላ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ የራሷን ማሻሻያ እና የውይይት ነጥቦች ዛሬ በፓኪስታን በኩል ለቴህራን ልካለች።
በአሁኑ ወቅት የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት የአሜሪካን ሰነድ በጥልቅ እየገመገሙት ሲሆን፣ እስካሁን ይፋዊ ምላሽ አልሰጡ፡ የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሞህሲን ናቅቪ በቴህራን የሚገኙ ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት
መካከል ያሉትን ሰፊ የሃሳብ ልዩነቶች ለማጥበብ እና ስምምነቱ እንዳይከሽፍ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት እያደረጉ ነው።
አሜሪካ በድርድሩ ወቅት የኢራን የዘይት ማዕቀብ እንዲነሳ ልትስማማ እንደምትችል ፍንጭ የሰጠች ቢሆንም፣ ኢራን ግን ሁሉንም ማዕቀቦች ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚያስገድድ ስምምነት እንዲሆን እየወተወተች ነው።
የቴህራን 14 ነጥብ እቅድ በዋናነት የሚያተኩረው ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ ለማቆም እና በአሜሪካ በኩል “የእምነት ግንባታ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በሚሉ ነጥቦች ላይ ነው።
@seledadotio

No comments yet.