አርሰናል ዋንጫ በልቶ አደረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ከረጅም ዓመታት ጥበቃ በኋላ መድፈኞቹ ዋንጫውን ማንሳታቸውን ማረጋገጣቸው ለክለቡ ትልቅ ታሪክ ነው!

ረዥም ዘመናት ጥበቃ እና ጉጉት ፍጻሜውን አግኝቷል። መድፈኞቹ ከአንድ ጨዋታ ቀሪነት ጋር የ2025/26 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ባለድል መሆናቸውን በይፋ አረጋግጠዋል።

​በ37ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ-ግብር ማክሰኞ ምሽት የተካሄደው የማንችስተር ሲቲ እና የቦርንማውዝ ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤ መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ሲቲዎች ከአርሰናል ጋር የነበራቸውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ሳይችሉ ቀርተዋል።

ይህም በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ የተቀመጠው አርሰናል በመጪው እሁድ የመጨረሻውን የሊግ ጨዋታውን ከክሪስታል ፓላስ ጋር ከመጫወቱ በፊት በአራት ነጥቦች ልዩነት ሊጉን እንዲያሸንፍ አስችሎታል።

​ይህ ድል ለአርሰናል ደጋፊዎች ታሪካዊ ነው፤ ክለቡ የመጨረሻውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ካነሳበት ከ2003/04 የ”ማይሸነፉት” (The Invincibles) ስኬታማ የውድድር ዓመት በኋላ ለ22 ዓመታት የናፈቀውን የሊግ ዘውድ ለመጀመሪያ ጊዜ የደፋበት ደማቅ ምሽት ሆኗል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#አርሰናል #የእንግሊዝፕሪሚየርሊግ #ሻምፒዮን #መድፈኞቹ #Arsenal #EPLChampions #COYG




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: