ኢትዮጵያ ቱኒዚያን አሸነፈች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋ ቱኒዚያ 1ለ0 አሸንፋለች።

አሚር ሚስባህ የኢትዮጵያን ግብ በጭማሪ ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል።

በመጀመሪያ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ከግብፅ ጋር አቻ ተለያይታ በአዘጋጇ ሞሮኮ ተሸንፋ የነበረችው ኢትዮጵያ አራት ነጥብ በመሰብሰብ በውድድሩ ቆይታለች።

በዚሁ ምድብ አንድ ሞሮኮ ግብፅን 2ለ1 በማሸነፍ በቀዳሚነት አጠናቃለች ፣ ተሸናፊዋ ግብፅ አራት ነጥብ ስትይዝ በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ በግብ ክፍያ ተበልጣ ሦስተኛ ደረጃ በማጠናቀቋ ወደ ዓለም ዋንጫው ለማለፍ በቀጣይ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ታከናውናለች።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2