የእስራኤል ፓርላማ ተበተነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ፓርላማው ራሱን ለማፍረስ የሚፈቅደውን አዋጅ ማጽደቁን አስታውቋል። ይህ ውሳኔ በእስራኤል ጠቅላላ ምርጫ እንዲካሄድ የሚያስገድድ ነው ተብሏል።

ይህም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁን በምርጫው የማሸነፋቸውን እድል ያጠበዋል የሚል ስጋት አሳድሯል።

የእስራኤል ህግ አውጭዎች 120 መቀመጫ ያለው የሀገሪቱ ፓርላማ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ያልተለመደ ውሳኔ ማሳለፋቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

ውሳኔው ከሳምንታት በኋላ የመጨረሻውን እውቅና ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላላ ምርጫ የሚደረግበት ቀንም በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል።

እስራኤል የመጨረሻውን ምርጫ ያደረገችው በ2022 ሲሆን፣ ቀጣዩ ምርጫ በሀማስ ጥቃት ምክንያት ተራዝሞ ቆይቷል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#reuters #ThiqahEth


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2