♦️
♦️ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እጩ በሆኑበት ምርጫ ክልል ከፍተኛ ህዝብ ለድጋፍ መውጣቱ ትኩረት ስቧል
በቅርቡ የፓን አፍሪካ ፓርላማ ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ዳግም ወደ ፓርላማ ለመመለስ በምረጡኝ ዘመቻና ቅስቀሳ ላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ እጩ በሆኑበትና እሳቸው በተገኙበት ጪሪ ምርጫ ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ አደባባይ በመውጣት እሳቸው ለወከሉት ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን አጋርነት አደባባይ በመውጣት አሳይተዋል።
በዚህም መድረክ ‘ንቃተ ህሊና’ን ጨምሮ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አጥናፉ ሃይሌና የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወንዱ አደመ ለሰልፉ ለታዳሚው ህዝብ መልእክት አስተላልፈዋል።
ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ስማቸው ከስፖርቱ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በሚወዳደሩበት የምርጫ ክልል በርካታ ደጋፊ መገኘቱ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)



Source: GetuTemesgen









No comments yet.