#EU : የአውሮፓ ኅብረት ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ ማንሳቱን አስታውቋል።” የኢትዮጵያ መ…

- Advertisement -
Sidebar AD
#EU : የአውሮፓ ኅብረት ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ ማንሳቱን አስታውቋል።
” የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ ነው ” በሚል በኢትዮጵያውያን ላይ የቪዛ ገደብ ተጥሎ ቆይቷል።
የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት አሁን ባወጣው መግለጫ፤ በኅብረቱ አባል አገራት ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በመለየት እና ወደ አገራቸው በመመለስ ረገድ መሻሻሎች ስለታዩ ገደቡ እንዲነሳ ተወስኗል።
ተጠሎ የነበረው እግዳ ምን ነበር ?
– አባል ሀገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) እንዳይችሉ፤
– የኅብረቱ አባል ሀገራት ከሁለት ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉ ፤
– የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛ የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱ፤
– መደበኛ ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ከፍ እንዲል … ተወስኖ ነበር።
አሁን ግን ይህ የቪዛ እገዳ ተነስቷል።
በሌላ በኩል፣ ከዚህ ቀደም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መስጠት አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ መልሶ አስጀምሯል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: