አሜሪካ የኢራን ዘይት የጫነች ማዕቀብ የተጣለባት “Skywave” መርከብን በህንድ ውቅያኖስ ላይ መያዟ ተሰማ!​የዎል ስትሪት ጆ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አሜሪካ የኢራን ዘይት የጫነች ማዕቀብ የተጣለባት “Skywave” መርከብን በህንድ ውቅያኖስ ላይ መያዟ ተሰማ!
​የዎል ስትሪት ጆርናል  የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የአሜሪካ ጦር ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላትን እና ማዕቀብ የተጣለባትን “Skywave” የተባለች የነዳጅ ጫኝ መርከብ በህንድ ውቅያኖስ ላይ በቁጥጥር ስር አውሏታል።
መርከቧ ባለፈው የካቲት ወር ላይ ከኢራኗ የኸርግ ደሴት  የተጫነ ከ1 ሚሊዮን በርሜል በላይ ድፍድፍ ዘይት ሳይዝ እንዳልቀረ ተገልጿል።Skywave” የተባለችው ይህች መርከብ የኢራንን ነዳጅ በማጓጓዝ ላይ በመሳተፏ ምክንያት ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአሜሪካ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተጥሎባት ነበር።
መርከቧ የማላካ ባህረ ሰላጤን አቋርጣ በማሌዥያ ምዕራባዊ የባህር ጠረፍ አካባቢ ስትጓዝ እንደነበር  የመርከብ መከታተያ መረጃዎች ያሳያሉ።

ይህ የአሜሪካ እርምጃ የመጣው በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል ያለው ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በረበበበት እና ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃቶችን ዳግም ለመጀመር በማስፈራራት ላይ ባሉበት ወቅት ነው።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: