— ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ
#Ethiopia | በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ዙሪያ “ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚና” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጋራ ያዘጋጁት ወሳኝ መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር፣ የዜጎችን የፖለቲካ ንቃት በማጎልበትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ስርዓት እንዲፈጠር በማድረግ ረገድ የማይተካ የሀገር ግንባታ አቅም አላቸው።
ሚኒስትር እናትዓለም አያይዘው እንደተናገሩት ሚዲያው የምርጫ ሂደቱን ግልጽነት እና ተጠያቂነት ባለው መልኩ በመከታተልና በመዘገብ፤ ሂደቱ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ታሪካዊ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል።
በቀሪዎቹ የምርጫ ቀናት ሁሉም የሚዲያ አካላትና ጋዜጠኞች ህዝብን የማንቃትና የማሳወቅ ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ በበኩላቸው፣ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህብረተሰቡን ዝግጁ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንና ይህ የአዳማው መድረክም የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ ሚኒስትር እናትዓለም መለሰን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የኢዜአ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ እንዲሁም በርካታ የሚዲያ አመራሮችና ጋዜጠኞች ታድመዋል።
#getu #EthiopianElection2018 #MediaRole #DemocracyEthiopia #AdamaForum #7thGeneralElection #EnaatAlemMelese #ENA #GovernmentCommunication #ሀገራዊምርጫ #የመገናኛብዙሃንሚና #አዳማ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen



Source: GetuTemesgen









No comments yet.