የምርጫ ጸሎት እና ዱአ ሊደረግ ነው!የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ፣ ሰባት የሃይማኖት ተቋማት የሚ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የምርጫ ጸሎት እና ዱአ ሊደረግ ነው!
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ፣ ሰባት የሃይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የጸሎት መርሀ ግብር ማዘገጀቱን መሆኑን አስታውቋል፡፡
ግንቦት 16/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ፓርክ በሚካሄው የምርጫ ጸሎት መርሀግብር ላይ ሰባት የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት አባቶች ባሉበት እንደሚከናወን ተገልጿል። በተመሳሳይ ሰዓት በሁሉም ክልሎች የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወንም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ገልጸዋል።
የአደባባይ ጸሎቱ በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በማሰብ የሚካሄድ መሆኑም የጉባኤው ጸሐፊ ገልጸዋል። ጉባኤው ያዘጋጀው መርሀግብር ከ1 ሺሕ በላይ ዜጎች የሚሳተፉበት የጸሎት እና የዱአ መርሃግብር መሆኑን ተናግረዋል፡፡(አንድ አፍታ)
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2