መረጃአዲሱ የታክስ አስተዳደር ሕግ፣ በግብይት ወቅት ደረሠኝ የማይቆርጡ ነጋዴዎች እስከ 100 ሺሕ ብር የሚደርስ  ቅጣት እንዲጣ…

- Advertisement -
Sidebar AD
መረጃ‼️
አዲሱ የታክስ አስተዳደር ሕግ፣ በግብይት ወቅት ደረሠኝ የማይቆርጡ ነጋዴዎች እስከ 100 ሺሕ ብር የሚደርስ  ቅጣት እንዲጣልባቸው የሚያዝ ኾኖ ተዘጋጀ።
ሸቀጦች የተሸጡበትን ዋጋ ኾነ ብሎ በመቀነስ ደረሠኝ መቁረጥም ተመሳሳይ ቅጣት ይጣልበታል።
አሁን በሥራ ላይ ባለው ሕግ፣ ነጋዴዎች ያለ ደረሠኝ በሚያካሂዱት እያንዳንዱ ግብይት የሚከፍሉት ቅጣት 50 ሺሕ ብር ነው።
አዲሱ ረቂቅ ሕግ፣ ደረሠኝ ባለመቁረጥ ባንድ ዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው ነጋዴዎች ድርጊቱን በድጋሚ ከፈጸሙ ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ እስር እንደሚቀጡም አስፍሯል።
በረቂቅ ሕጉ ላይ ትናንት ምክክር ያደረጉ ባለድርሻ አካላት፣ የገንዘብ ቅጣቱ የተጋነነ መኾኑን በመጥቀስ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: