#FastMereja I 1447ኛው የኢድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል ረቡዕ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በመላው ሀገሪቱ በድምቀት እንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታውቋል። ፍርድ ቤቱ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የዘንድሮውን የዓረፋ በዓል አቆጣጠር በተመለከተ በሰጠው መግለጫ መሠረት፣ የታላቁ ሐጂ ሥነ-ሥርዓት ዋና ቀን (ውቅፉ ዓረፋ) የፊታችን ማክሰኞ ዙልሒጃ 9 ቀን ይውላል። ይህንን ተከትሎም ማግስቱን ረቡዕ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም 1447ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ እንደሚውል ፍርድ ቤቱ በይፋ አድርጓል።
Source: FastMereja









No comments yet.