የ12ኛ ክፍል ፈተና በሙሉ በበይነ መረብ ይሰጣል ቢባልም ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተማሪዎች በወረቀት ይፈተናሉ። ከሰኔ 24 እስ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የ12ኛ ክፍል ፈተና በሙሉ በበይነ መረብ ይሰጣል ቢባልም ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተማሪዎች በወረቀት ይፈተናሉ።
 
ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 564 ሺህ 219 ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በ667 የፈተና ማዕከላት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል ።
 
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ እንደገለጹት፥ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በ97 ዩኒቨርሲቲዎች እና በ570 የክልል ማዕከላት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
 
ፈተናውን በሙሉ አቅም በበይነ መረብ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በተለያዩ ምክንያቶች ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎች እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።
በየክልሎች እና የፈተና ማዕከላት ያለው አቅም የተለያየ ቢሆንም በርካታ ኮምፒዩተሮች ለፈተና ዝግጁ እየተደረጉ ይገኛል፡፡
ተማሪዎች የፈተና ስርዓቱን እንዲለማመዱና ትምህርት ቤቶች እና ወላጆች ለተፈታኝ ተማሪዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2