በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

- Advertisement -
Sidebar AD

ዮናታን ከድር፣ ደረሰ ኃይሉና አብደላ በድር የተባሉት ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ/ም በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ ፉሪ ኮንዶሚኒየም አካባቢ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሟች ኪሩቤል ከበደ የተባለውን ስራ አለ በሚል በስልክ በመጥራት አንገቱን አንቀው ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡

አስከሬኑንም በፕላስተርና በላስቲክ በጠቅለል በልብስ መያዣ ሻንጣ ውስጥ በመክተት የሟችን የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 50945 D4D ፒካፕ ተሽከርካሪ በመያዝ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 ሠዓት አካባቢ ለዕይታ ተጋላጭ በማይሆኑበት ቆጣሪ ኮንዶሚኒየም አካባቢ አስከሬኑን ጥለው ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከሟች ላይ የወሰዱትን ሳምሰንግ አልትራ 21 ተንቀሳቃሽ ስልክና ተሽከርካሪውን ይዘው ወደ ሳሪስ በመጓዝ ብሔረ ፅጌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተሽከርካሪው ሞተር በመጥፋቱና በማስቸገሩ በአካባቢው በሚገኝ የመኪና ማሳደሪያ ቦታ በማቆም የሟችን ስልክ በመሸጥ ራሳቸውን ደብቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርመራና የክትትል ቡድኑ የወንጀል ድርጊቱ መፈፀም መረጃ ከደረሰው በኋላ 24/7 ያላሰለሰ ብርቱ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የምርመራና የክትትል ቡድኑ ከሟች ጋር ተያያዥነት ሊኖራቸው ይችላል ባላቸው መረጃዎች ላይ ሰፊ ጥናትና ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን የመለየት እንዲሁም ከአድካሚ ክትትል በኋላ በቁጥጥር ስር የማዋል ተግሩንም በድንቅ ብቃት ፈጽሟል፡፡

በዚህ የግድያ ወንጀል የክትትል ስራ ውስጥ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እንዲሁም ህብረተሰቡ ላደረገው ድጋፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

Addis Ababa police






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1