የኢትዮጵያ አባቶች ቀን ክብር ለአባትነት በሚል መሪ ቃል ተከበረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሀገራችን በየዓመቱ ግንቦት 15 ቀን የሚከበረው የኢትዮጵያ አባቶች ቀን ዘንድሮም ክብር ለአባትነት በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።

ይህ መርሃ ግብር መከበር የጀመረው ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ቀኑ የተመረጠበት ዋና ምክንያትም ቀደምት አባቶቻችን የፋሽስት ጣሊያን ወራሪ ኃይልን በአድዋ ምድር ድል አድርገው በክብር ወደ መናገሻ ከተማቸው የተመለሱበትን ታሪካዊ እለት ለመዘከር ታስቦ ነው።

ቀኑ ታሪክ ሰርተው ያለፉትን ወላጆቻችንን ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ዛሬም በፈተና ውስጥ ሆነው ለሀገርና ለትውልድ ዋስትና ለሆኑት የዘመናችን አባቶች እውቅና የምንሰጥበት ጭምር ነው።

አባትነት ከስጋ ዝምድና ባለፈ በትውልድ ላይ የሚኖርን ዘላቂ ኃላፊነት፣ መስዋዕትነት እና ፍቅርን ያቀፈ ጥልቅ ትርጉም አለው።

አባት የቤት ድምቀት፣ የመሪነት ተምሳሌት፣ የታሪክና ቅርሥ አሻጋሪ እንዲሁም የጽናት ማማ ነው። ቁጥር ሥፍር የሌላቸው አባቶች መከራና ችግራቸውን በውስጣቸው ደብቀው ለልጆቻቸው ሕይወት ሲሉ ራሳቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ። እነዚህን ውድ አባቶች ዘወትር ልናመሰግናቸውና ልናከብራቸው ይገባል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት አባትነት እጅግ የበዛ መራራ ፈተና ሆኖባቸዋል።

አያሌ አባቶች ከራሳቸው አልፎ በቤተሰቦቻቸው ላይ የሚደርሰውን ስደትና ሰቆቃ መመልከት እያቃታቸው ይገኛል።

ለዓመታት ከኖሩበት ቀዬ መፈናቀል፣ የኑሮ ውድነት እና የገቢ አለመጣጣም አባቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳቀቃቸው ነው።

በመሆኑም ተስፋቸውን ለተነጠቁ፣ የድካማቸውን ፍሬ በአንድ ጀምበር አጥተው መንገድ ላይ ለቀሩ አባቶች ዛሬ ደራሽና መጽናኛ ልንሆናቸው ይገባል።

ትናንት ለሌሎች ይተርፉ የነበሩትን አባቶቻችንን ዛሬ ልናስባቸውና ከጎናቸው ልንቆምላቸው ይገባል።

የኢትዮጵያ አባቶች ቀን በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራች እዮብ አርጋው ተሰማ እንደገለጹት፣ አባቶች ለልጆቻቸው የከፈሉት መስዋዕትነት በቃላት የሚገለጽ ባይሆንም በልባችን መዝገብ ሁልጊዜም በክብር ይኖራል።

ለአባቶች የሚደረገው ክብርና ምስጋና ምንጊዜም ሕያው ሆኖ ይቀጥላል።

#የአባቶችቀን #የኢትዮጵያአባቶች #አባትነት #ታሪክ #ክብር ለአባቶች #በጎአድራጎት
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: