#Ethiopia | የንፋስ ስልክ ላፍቶው አሰቃቂ ግድያ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፉሪ ኮንዶሚኒየም አካባቢ ስራ እንደተገኘለት በመግለጽ በስልክ የተጠራውን ወጣት ኪሩቤል ከበደ አንገቱን በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረጉ ሦስት ግድያ ፈጻሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
ዮናታን ከድር፣ ደረሰ ኃይሉ እና አብደላ በድር የተባሉት እነዚህ ተጠርጣሪዎች የወጣቱን ህይወት ካጠፉ በኋላ አስከሬኑን በላስቲክና በባለቀለም ፕላስተር በመጠቅለል በሻንጣ ውስጥ ከተውት ነበር።
ተጠርጣሪዎቹ የሟቹን አስከሬን በራሱ መኪና ውስጥ በመጫን ቆጣሪ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጥለውት የተሰወሩ ሲሆን ከሟች ላይ የዘረፉትን ሳምሰንግ አልትራ 21 የሞባይል ስልክ በመሸጥና መኪናውን ደግሞ ብሔረ ፅጌ አካባቢ በማቆም ራሳቸውን ደብቀው ቆይተዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቡድን ይህንን ዘግናኝ የወንጀል ድርጊት ከተረዳበት ጊዜ ጀምሮ ሌት ከቀን ባደረገው ያላሰለሰና ጥብቅ ክትትል ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉ ገልጿል።
#የአዲስአበባፖሊስ #የወንጀልምርመራ #ደህንነት #ፍትህ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.