መምህራንን የሚያግዝ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ( #AI ) ስርዓት ለመዘርጋት በሙከራ ላይ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡

- Advertisement -
Sidebar AD

መምህራንን የሚያግዝ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ( #AI ) ስርዓት ለመዘርጋት በሙከራ ላይ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

ወሬው የተሰማው በቅርቡ ህዋዌ ኢትዮጵያ በሳናዳው የትምህርት ጉባኤ ላይ ሲሆን በመድረኩም የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ፖሊሲ አውጭዎች፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ሌሎች ከትምህርት ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ተቋመት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ AI እና ዲጂታል መሠረተ ልማት ያላቸው ሚና ምን አንደሚመስል ውይይት ተደርጓል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ስርዓቱን በዲጂታል መንገድ ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ አንደሆነ በጉበኤው ላይ አስረድቷል፡፡

ከእነዚህ ስራዎች መከካል አንደኛው መምህራንን የሚያግዝ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI ) ስርዓት መዘርጋት መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

መምህራንን የትምህርት እቅድ በማውጣት፣ፈተና በማዘጋጀት በመሳሰሉት ጉዳዩች አንዲያግዝ ተብሎ በሙከራ ላይ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ስርዓት በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓትወይንም ካሪኩለምን መሰረት አድርጎ የተሰናዳ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ስርዓቱ በመተግበሪያ ወይንም አፕሊካሽን የተዘጋጀ ሲሆን አንድ ጊዜ በኮምፒውተር ላይ ከተጫነ ያለ ኢንተርኔትም መስራት ይችላል ሲሉ በትምህርት ሚኒስቴር የኢ-ለርኒንግ አስተባባሪ አቶ ሙሉነህ አጥናፉ ነግረውናል፡፡

በተወሰኑ የመጀመሪያ ደረጃ ተምህርት ቤቶች ላይ በሙከራ ላይ የሚገኘው ይህ ፕሮግራም ውጤቱ ታይቶ ወደፊት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ ለመተግበር እቅድ መኖሩንም ሰምተናል፡፡

ይህን በሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI) የታገዘ የዲጂታል የትምህርት ስርዓት መጀመር ያስፈለገው የመምህራንን አቅም ለማጎልበት፣ ተማሪዎችንም በመማሪያ መጻህፍት ምክያንት የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ አንደኛው መንገድ ይህ በመሆኑ ነው ሲሉ አቶ ሙሉነህ አጥናፉ አስረድተዋል፡፡

ህዋዌ ኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓቱን በቴክኖሎጂ ለማገዝ አንሰራ አንደሆነ በጉባኤው ላይ ተናግሯል፡፡

በቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና በትምህርት ተቋማት መካከል የተጠናከረ ትብብር መኖር የኢትዮጵያን ትምህርት በዲጂታል ስርዓት ለመደገፍ እንደሚያግ ህዋዌ ተናግሮ፣ለዚህም አንደሚሰራ አስረድቷል፡፡

ኩባንያው በዲጂታል ስልጠና እና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ በኩል የኢትይጵያ ትምህርት በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በመድረግ ላይ ያለውን ተሳትፎ አንደሚቀጥል በሃላፊዎቹ በኩል አረጋግጧል፡፡

Sheger Fm


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: