በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የባልትና ዕቃ የሚገዙ በመምሰል ሞባይል ስልክ ስርቆት ሲፈፅሙ የነበሩ 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋ

- Advertisement -
Sidebar AD

በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የባልትና ዕቃ የሚገዙ በመምሰል ሞባይል ስልክ ስርቆት ሲፈፅሙ የነበሩ 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ተጠርጣሪዎች መቅደስ ተስፋዬ፣ ያሬድ ሙሉጌታ እና ኤፍሬም አብርሀሌ የተባሉ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አርባ ዘጠኝ ሎሚ ከለር የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A 73615 አ/አ የሆነ ቪትስ ተሽከርካሪ በመጠቀም በክፍለ ከተማው የተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ባልትና መሸጫ ቤቶችና ብቻቸውን የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን በመከታተል ሞባይል ስልኮችን በመቀማትና በመስረቅ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸው በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ እንደለመዱት ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ/ም በክፍለ ከተማው ወረዳ 5 አርባ ዘጠኝ ሎሚ ከለር የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ከሚገኝ ባልትና መሸጫ ሱቅ በመሄድ የዋጋ ግምቱ 45000 ሺህ ብር የሚሆን ሞባይል ስልክ ሰርቀው በተሽከርካሪያቸው ሊያመልጡ ሲሉ በአካባቢው በነበሩ የወንጀል መከላከል የፖሊስ አባላትና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ በተሽከርካሪው ውስጥ ባደረገው ፍተሻ የተለያየ ሞዴል ያላቸው 4 ሞባይል ስልኮች የተገኙ ሲሆን በግለሰቦቹ ወንጀል የተፈጸመባቸው ዜጎች ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ንብረታቸውን መምረጥና መረጃ መስጠት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

የወንጀል አፈፃፀም ከጊዜ ወደ ጊዜ መልኩን እየቀየረ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በአፋጣኝ ለፖሊስ መረጃ መስጠት እንደሚገባም መልዕክት ተላልፏል፡፡

Addis Ababa police


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2