በአፍሪካ ፖለቲካና በሳይንስ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው አዲሱ የምርምር መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በዶክተር ማቲዎስ ጌና የተሰናዳውና ላለፉት ሦስት ዓመታት ሰፊ ዝግጅት የተደረገበት ነገረ እርግማን ወበረከት የተሰኘው አዲስ የምርምር መጽሐፍ ነገ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ በደመቀ ሁኔታ ይመረቃል።

ይህ አዲስ የንባብ መዓድ ምንም እንኳን ሃይማኖታዊ ይዘት ቢኖረውም ሁሉንም የሕይወት ዘርፎች የሚዳስስ ሲሆን በስድስት ዋና ዋና አበይት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።

በተለይም በተለያዩ እምነቶች፣ በሥነ ልቦና፣ በባህልና በማኅበራዊ ግንኙነቶች ዙሪያ ሰፊ ትንታኔ ያቀርባል።

በተጨማሪም በሳይንስ እንዲሁም በኢትዮጵያና በአጠቃላይ በአፍሪካ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የእርግማን እና የበረከት አስተዋጽኦ ምን እንደሚመስል በጥናት ላይ ተመስርቶ የሚተነትን በመሆኑ በአንባቢያን ዘንድ ትልቅ ጉጉትን አሳድሯል።

የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በሚገኙበት በዚህ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የመጽሐፉ ምረቃ ለሕዝብ ክፍት የሚሆን ሲሆን የመጽሐፉ ደራሲ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ በጥናትና ምርምር ዘርፍ ላይ በንቃት እየሰሩ የሚገኙ አንጋፋ ባለሙያ ናቸው።

#መጽሐፍ #ምረቃ #ምርምር #ሳይንስ #ፖለቲካ #አፍሪካ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: