ዳሪክ ኢቨንት እና ኪንግስ ፉትቦል በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የዝግጅት አሰናጅ ድርጅት የሆነው ዳሪክ ኢቨንት እና የኪንግስ እግር ኳስ ቡድን፣ የእግር ኳስ ዝግጅቶችን ከዝማሬ አምልኮ ጋር አቀናጅተው ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራረሙ።

ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሆን የተለያዩ ስፖርታዊ እና መንፈሳዊ ኩነቶችን ለማዘጋጀት የሚያስችላቸውን ትብብር የፈጠረ ነው።

​በፍጹም አምባቸው (ኩቺ) የሚመራው ዳሪክ ኢቨንት፣ ክርስቲያናዊ ዝግጅቶችን በአማረ ሁኔታ በማስተናገድ የሚታወቅ ተቋም ነው። ስምምነቱን በዳሪክ ኢቨንት በኩል ፍጹም አምባቸው፣ ከኪንግስ እግር ኳስ ቡድን በኩል ደግሞ የቡድኑ መሪ ዘማሪ አቤኔዜር ሰብስቤ በመፈረም አጽድቀውታል።

​በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይ ካቦድ የዝማሬ አገልግሎት እንደ አባሪ ተቋም የተገኘ ሲሆን፣ በኩሪፍቱ ቃለ ሕይወት ግቢ በተከናወነው የፊርማ ስነስርዓት ላይ የሁለቱም ተቋማት አጋፋሪዎች እና አባላት ተገኝተዋል።

ይህ ትብብር ወደፊት የሚከናወኑ ስፖርታዊ እና መንፈሳዊ ዝግጅቶችን በይበልጥ ለማሳደግ እና ለታዳሚው ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: