#Ethiopia | ”ምስጉን ሰው” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የአቶ ታምራት ተመስገን የሕይወት እና የሥራ ታሪክ የሚተርክ መጽሐፍ፣ እሑድ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በዲ ሊዮፖል ሆቴል የክብር እንግዶች፣ አንጋፋና ዕውቅ የሥነጽሑፍ ሰዎች፣ የባለታሪኩ ወዳጆች እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት ይመረቃል።
ባለታሪኩ አቶ ታምራት ተመስገን የተወለደው በጉራጌ ዞን በእንደጋኝ ወረዳ ሲሆን፣ ሊስትሮ እና ሌሎች እጅግ አነስተኛ የሆኑ ሥራዎችን ከመሥራት ተነስቶ ራሱን በብዙ ትግሎች በማብቃት፣ ሀገሪቱ አሉኝ ከምትላቸው የግንባታ ኮንትራክተሮች አንዱ ለመሆን ከመብቃቱም በተጨማሪ ለበርካቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ በሙያው እንዲበቁና ራሳቸውን በከፍተኛ ደረጃ እንዲያሳድጉ አድርጓል፡፡
ባለ ታሪኩ ከጠንካራ ሠራተኛነቱ ባለፈም በበርካታ የበጎ እና ማኅበረሰባዊ ሥራዎቹ ይታወቃል። በዚህም በችግር የተዘጉ በርካታ ቤቶችን ከፍቷል፤ አቅመ ደካሞችን አግዟል፤ የታመሙትን አሳክሟል፡፡ መንገዶችን፣ ቤተ እምነቶችን፣ ቤተ ሕክምናዎችን፣ ት/ቤቶችን በሙያውም በገንዘቡም በብዙ ደግፏል፡፡ ገንብቶም ለአገልግሎት እንዲውሉ አድርጓል፡፡
“ምስጉን ሰው” በመጽሐፍ 5 ክፍሎች፣ በ42 ምዕራፎች እና በ382 ገጾች የቀረበ ሲሆን፣ የተዘጋጀውም በሃያሲና የሥነጽሑፍ መምህር ባዩልኝ አያሌው እና በደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ አማካይነት ነው።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.