አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሚዲያ ተቋማት በጥናት ላይ የተመሰረቱ ይዘቶችን እንዲያቀርቡና አርካይቮቻቸውን ለትውልድ ግንባታ እንዲ

- Advertisement -
Sidebar AD

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሚዲያ ተቋማት በጥናት ላይ የተመሰረቱ ይዘቶችን እንዲያቀርቡና አርካይቮቻቸውን ለትውልድ ግንባታ እንዲያውሉ ጥሪ አቀረቡ

#Ethiopia | የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል እንዲሁም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በጥናት የተደገፉ የይዘት ዝግጅቶችን እንዲያቀርቡ አሳሰቡ።

ተቋማቱ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዘ ጥራት ያለው መረጃ ለህዝብ ተደራሽ ማድረግና ያላቸውን ውድ የአርካይቭ ሀብት ለትውልድ ግንባታ ማዋል እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ አመራሮች በሰብሳቢያቸው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መሪነት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

ባለስልጣኑ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሚዲያዎችን የመቆጣጠር፣ የመደገፍ፣ በመካከላቸው መልካም የስራ ግንኙነት እንዲጠናከር የማድረግ እና በስርጭታቸው የሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም እንዲጠበቅ የመስራት ኃላፊነት አለበት።

አምባሳደር ሬድዋን በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን በጥናትና ምርምር ላይ የተመሠረቱ ጥራት ያላቸው ስራዎችን ለማቅረብና የዲጂታል ሚዲያውን ዘርፍ ለማጠናከር የጀመረው ጉዞ ተስፋ ሰጪና የሚበረታታ ነው።

ይህንን በጎ ስራ ይበልጥ ለማሳደግና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ በተቋሙ ውስጥ ሁልጊዜም እንቅልፍ አልባ ሥራ እና ቀጣይነት ያለው የፈጠራ አስተሳሰብ ሊኖር እንደሚገባ በአጽንኦት አስገንዝበዋል።

ኢቢኤስ ቴሌቪዥንም በራሱ ልዩ የአቀራረብ ስልት ለዓመታት አዝናኝና መልዕክት አዘል ፕሮግራሞችን ሲያቀርብ መቆየቱን የገለጹት አምባሳደሩ፣ በቀጣይም በፈጠራ የታጀቡና ኢትዮጵያዊ እሴቶችን የሚያንጸባርቁ ይዘቶችን በማዘጋጀት በአገሪቱ የሜዲያ መስክ ያለውን አዎንታዊ ሚና አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ በበኩላቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሚዲያዎች በምርምር የተደገፉ የይዘት ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው ቀደም ሲል ማሳሰባቸውን አስታውሰዋል።

የኢቢሲ አሁናዊ አሰራር የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም፣ ደህንነት፣ ብዝሃነትና ልማትን ያማከሉ አጀንዳዎችን በጥራት ለማቅረብ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

የሀሰተኛ መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮች መስፋፋት በሆነበት በዚህ የዲጂታል ዘመን፣ ብሔራዊ ሚዲያው ፈጣንና ተዓማኒ መረጃን በማቅረብ ረገድ ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ጠቅሰዋል።

አክለውም በሁለቱም ሚዲያዎች የዲጂታል እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ መረጃዎችን ተደራሽነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#መገናኛብዙሃን #ሬድዋንሁሴን #ኢቢሲ #ኢቢኤስ #ቴክኖሎጂ #አርካይቭ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: