#Ethiopia | ታሪክን ለትውልድ የማሻገር ተራው የእኔ ነው በሚል መሪ ቃል ሰፊ እድሳት እየተደረገለት የሚገኘው የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የቀሩትን የግንባታ ስራዎች ለማጠናቀቅ እንዲቻል መላው ኢትዮጵያውያን የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።
በአዲስ አበባ ከተማ እምብርት ላይ የሚገኘው ይህ ታሪካዊ የእምነት ተቋም ከተመሰረተ 130 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ልዩ በሆነው የስነ ህንጻ ጥበቡና የቅርስነት እሴቱ ይታወቃል።
የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ክብሩ ገብረ ጻድቅ እንደገለጹት የቅርስ ጥገና ስራው ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ የገንዘብ አቅምን ለማጠናከር ከግንቦት 28 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የኢንተርኔት ወይም የበይነ መረብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።
ይህ ታሪካዊ ህንጻ ባለፉት ረጅም ዘመናት በርካታ ፈተናዎችን አልፎ መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ጉዳት ደርሶበታል።
በተለይም በህንጻው ውስጥ የተከሰተው የውሃ ስርገት፣ የውጪው ግድግዳ መወየብ እንዲሁም ያለምንም የብረት ድጋፍ በቀይ ሸክላ ብቻ የተገነባው ልዩ የኮርኒስ አካል መሰንጠቅና ከጉልላቱ ጀምሮ የሚፈሰው ዝናብ ህንጻውን ለአደጋ በመዳረጉ አሁን ላይ የተጀመረው እድሳት የግድ አስፈላጊ መሆኑን አስተዳዳሪው አብራርተዋል።
በበይነ መረብ በሚካሄደው በዚህ መርሃ ግብር ከ250 እስከ 300 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን መላው ምዕመን የበረከቱ ተሳታፊ በመሆን በገንዘብ፣ በጉልበትና በማቴሪያል ክርስቲያናዊና ሀገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠይቋል።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ በሁሉም ባንኮች በኩል 1423 የተባለውን አጭር የሂሳብ ቁጥር በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ የሚቻልበት አሰራር ተመቻችቷል።
በተጨማሪም የቤተክርስቲያኑ የጉልላት ስራ በመጠናቀቁ እሁድ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ታላቅ የመስቀል መልሶ ማስቀመጥ ስነ ስርዓት የሚከናወን በመሆኑ ህዝበ ክርስቲያኑ በቦታው ተገኝቶ በሂደቱ ላይ እንዲሳተፍና የበኩሉን እገዛ እንዲያደርግ አስተዳዳሪው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#ቤተክርስቲያን #ቅርስ #እድሳት #የገቢማሰባሰቢያ #ታሪክ #ሃይማኖት #ዜና #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.