ልደት እና ሞት በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ 5 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ሊጣል ነው
የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚቀጥለው በጀት ዓመት (ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም.) ጀምሮ እንደ ልደት እና ሞት ያሉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎችን በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ የ5 ሺሕ ብር ቅጣት ሊጥል እንደሚችል አስታውቋል።
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ የማኅበረሰቡን የግንዛቤ ማነስ ከግምት ውስጥ በማስገባት እስካሁን አስገዳጅ የቅጣት ውሳኔዎች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን ገልጸው፣ አሁን ግን ደንቡን ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል።
እንደ አቶ ጥጋቡ ማብራሪያ፤ ማንኛውም ነዋሪ፦
👉ልደትን ፦ በ90 ቀናት ውስጥ
👉ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት እና ጉድፈቻ ኩነቶችን ፦ በ30 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ ግዴታ አለበት።
ነዋሪዎች የተቀመጠውን የጊዜ ቀነ-ገደብ በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውን ካልተፈለገ የገንዘብ ቅጣት እንዲጠብቁም ኤጀንሲው አሳስቧል።
ምንጭ: አሐዱ ራዲዮ
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.