በታሪካዊው መለያ ምት ተሸንፈናል!የዓለም ዋንጫ ህልማችን በመለያ ምት (Penalties) መክኗል! የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች…

- Advertisement -
Sidebar AD
በታሪካዊው መለያ ምት ተሸንፈናል!
የዓለም ዋንጫ ህልማችን በመለያ ምት (Penalties) መክኗል! የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች (U-17) ብሔራዊ ቡድን ወደ ዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከሞዛምቢክ ጋር ያደረገውን ወሳኝ ፍልሚያ በሙሉ ሰዓት 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ካጠናቀቀ በኋላ፣ በተሰጠው መለያ ምት 5 ለ 4 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ከኳታሩ የዓለም ዋንጫ ውጪ ሆኗል።
በጨዋታው መጀመሪያ 16ኛው ደቂቃ ላይ በአሚር ሚስባህ አስደናቂ ግብ መሪ መሆን ብንችልም፣ ጨዋታው 1-1 ተጠናቆ ወደ መለያ ምት ማምራቱ ይታወሳል።
በመጨረሻም ዕድል ከእኛ ጋር ባለመሆኗ በጠባብ ውጤት ታሪካዊውን ጉዞ አጠናቀናል።
ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ማለፍ ባንችልም፣ እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ አረንጓዴ፣ ቢጫ, ቀይ ሰንደቅ ዓላማችንን አንስተው ተስፋ የሰጡን፣ አንገታቸውን ቀና አድርገው የተፋለሙት ጀግኖቻችን ኩራቶቻችን ናቸው!
እስከዚህ ደረጃ ለደረሰው ድንቅ ስብስብና ለአሰልጣኞች በሙሉ ምስጋና ይገባቸዋል።
የወደፊቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተስፋዎች እነዚህ ልጆች ናቸውና ወደፊት ከዚህ የተሻለ ታሪክ እንደሚሰሩ አንጠራጠርም! ህልሙ እዚህ አያበቃም!
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2