በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ቡኖ ማላ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በዲላ ኢንዱስትሪያል ፖርክ ተከፈተ።
የጌዴኦን የቡና እና ሥጋ ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የዲላን የኢንቨስትመንት የሥበት ማዕከልነት ከፍ ለማድረግና የቱሪዝም መዳረሻዎቹን ለዓለም በስፋት ለማሳየት ያለመው ይህ ግዙፍ መድረክ ዛሬ ከቀኑ 9:00 በዲላ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲከፈት የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች የጌዴኦ ዞንና የዲላ ከተማ አመራሮች እና በርካታ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ኤክስፖው በነገው እለትም በበርካታ ባለድርሻ አካላት እየተጎበኘ በኪነ-ጥበባትና መዝናኛ ዝግጅቶች እየተዋዛ እስከ አመሻሽ እንደሚቀጥል ተገልጿል።



Source: FastMereja









No comments yet.