“የኢቦላ ቫይረስ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው” – WHOየዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የኢቦላ ቫይረስ አደጋ “አደገኛ ነው” አለ። …

- Advertisement -
Sidebar AD
“የኢቦላ ቫይረስ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው” – WHO

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የኢቦላ ቫይረስ አደጋ “አደገኛ ነው” አለ። ድርጅቱ ወረርሽኙ በዲሞክራቲክ ኮንጎ በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሚገኝ ገልጿል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም “በሀገር አቀፍ፣ ቀጠናዊና ዓለማቀፍ ደረጃ ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ እየገመገምን ነው” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ፣ “ኮንጎ ውስጥ እስካሁን  177 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፣ 750 በሻይረሱ ተይዘዋል” ብለዋል።
አክለው፣ “በኡጋንዳ የተመዘገበ ሞትም ሆነ ተጠርጣሪ የለም” ሲሉ ተናግረዋል።
እንዲሁም፣ በዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ጤና ስጋት ምላሽ ዳይሬክተር አብዱረህማን መሐመድ፣ “የኢቦላ ቫይረስ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው” ብለዋል።
“ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያገለግል እውቅና የተሰጠው ክትባት የለም” ሲሉም ገልጸዋል። #france24
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2