ከአንድ መኖሪያ ቤት በአጥር ዘሎ በመግባት ብስክሌት የሰረቀው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ።

- Advertisement -
Sidebar AD

ፈረጃ ዳኛቸው የተባለው ተከሳሽ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አካባቢ ከሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው።

ግለሰቡ ከለሊቱ በግምት 8፡00 ሰዓት ገደማ ከግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ግቢ በአጥር ላይ ዘሎ በመግባት ተቀምጠው ከነበሩ ብስክሌቶች ውስጥ 45 ሺህ ብር የሚያወጣን አንድ ብስክሌት ሰርቆ ለመውጣት ሲሞክር በግቢው አጥር ላይ ተገጥሞ የነበረ አላርም ድምፅ ማሰማቱን ተከትሎ የግል ተበዳይም የይድረሱልኝ ጥሪ በማሰማታቸው አካባቢው ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላትና የቅጥር ጥበቃዎች ትብብር እጅ ከፈንጅ ተይዞ ንብረታቸው መመለሱን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአውጉስታ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል፡፡

በተከሳሽ ፈረጃ ዳኛቸው ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማጣራት መዝገቡን ለአቃቤ ህግ በመላክ ክስ እንደተመሰረተበት ያስታወቀው ፖሊስ ጣቢያው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎትም ፈረጃ ዳኛቸውን ጥፋተኝነቱን በሰው ማስረጃ በማረጋገጥ ተከሳሽን ያስተምራል ሌሎችን ያስጠነቅቃል ሲል ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ፈጣን ችሎት በ5 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ እንዳስተላለፈበት ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ጨለማን ተገን አድርገው ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች ቀን ቀን ጥናት አድርገው በመሆኑ ህብረተሰቡ በየአካባቢው ላይ የማያውቁት ፀጉር ልውጥ ሰው አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲያሳይ ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሰል ወንጀልን ለመከላከል የአካባቢ ቅጥር ጥበቃ ከመቅጠር ጀምሮ ህብረተሰቡ ለንብረቱ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም መልዕክት ተላልፏል፡፡

Addis Ababa police



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1