ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ እና ባለቤቱ ቢታንያ በሰይፉ_ሾው ያደረጉት አስገራሚ ቆይታ እና ያልተሰሙ እውነታዎች!

- Advertisement -
Sidebar AD

💍💕

#Ethiopia | ታዋቂው ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ እና ውብ ባለቤቱ ቢታንያ በሰይፉ ሾው ቀርበው ስለ ፍቅራቸው፣ ስለ ትዳራቸው እና ስለ ህይወታቸው ጣፋጭና አስቂኝ ገጠመኞችን አካፍለዋል። ከቆይታቸው የተወሰዱ ድንቅ ነጥቦች እነሆ፦

🎙 ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ…

* ⚽️ “የሰርጌ ቀን አርሰናል ዋንጫ ካልበላ አላገባም ብዬ ነበር!”

* 📺 “ሚዲያ ላይ ስለማታውቀኝ ነው የጠቀመኝ፤ ለእኔ እሷን ለማጥናት 6 ወር በቂ ነበር። ከውበቷ ውጪ አስተሳሰቧ ‘ውይ’ የሚያስብል ነው፤ በትውውቅ 4 ዓመት ሆኖናል።”

* 🎬 “ማስታወቂያ እንድትሰራ እኔ ነኝ በግድ ያስገባኋት፤ ፈጣሪ የሰጣትን ቁንጅና እና አቋም መጠቀም አለባት።”

* 👩‍ያ “እናትዬ ብዬ ነው የምጠራት።”

* 💼 “በጋዜጠኝነት ደመወዝ ብቻ ልትኖር አትችልም። ስራ እወዳለሁ፤ የተለያዩ ኢቨንቶችን እሰራለሁ።”

* 🍲 “የማይሰለቸኝ ምግብ ሽሮ ነው።”

* 📺 “ቀጥታ ስርጭት ዜና እያነበብኩኝ ወንበሩ ሰምጦብኝ ያውቃል! ካሜራ ማናችንም ከነካሜራው ከአውሮፕላን ላይ ወድቆብናል።”

* 🎶 “የሀገር ካስማ ከተሰኘው ዘፈን ፕሮዲውሰሮች አንዱ ነበርኩኝ። የቴዲ ታደሰን ‘በቸር ይደር’ እና የጥላሁንን ‘አምሳሉ’ ዘፈኖችን እወዳለሁ።”

* ⛰ “ጊሸን ሄጄ እንደመጣሁ ነው ፀሎቴ የሰመረልኝ። መስከረም 21 እኔም እናቴም የተወለድንበት ቀን ነው።”

* 🎤 “የሰርጌ ቀን ድምፃዊ ጎሳዬ፣ አብነት እና ዳዊት ይኖራሉ።”

👸 ባለቤቱ ቢታንያ …

* 🏪 “እኔ ሱቅ እቃ ሊገዛ መጥቶ ነው የተዋወቅነው። ሰዎች እስኪነግሩኝ ድረስ ጋዜጠኛ መሆኑን አላውቅም ነበር።”

* 💍 “የ’ታገቢኛለሽ’ ሰርፕራይዙ በጣም ደስ ይል ነበር።”

* 🐕 “አዳነ ውሻ አምጥቶልኝ ሰርፕራይዝ አድርጎኛል። ‘አባትዬ’ ብዬ ነው የምጠራው።”

* 👩‍❤️‍👨 “አዳነ ፍቅር መስጠት ይችላል፤ የተካነበት ነው። ልክ እንደ አባቴ አይነት ባል ነው ያገኘሁት።”

* 💭 “ሰዎች ተጋብተው ከሚጣሉ ይልቅ መጀመሪያ ተጣልተው ነው መጋባት ያለባቸው።”

* 🥩 “ጥሬ ስጋ እና ጭኮ እወዳለሁ፤ የንዋይ ደበበን ‘አሜን’ ዘፈን እመርጣለሁ።”

* 📱 “የእድል ቁጥሬ 6 ስለሆነ 6 ልጆች ቢኖሩኝ ደስ ይለኛል!

የአዴ እና የቢቱ ፍቅር ፍጻሜው ለሰርግ በቃ! አዴ አንተ ሰው አክባሪና ትሁት ጋዜጠኛ እንኳን ደስ አለህ። ለሁለታችሁም ዘላቂና ደስተኛ የትዳር ዘመን እንመኛለን! 🥂🎉

Via Zerihun Teznanu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: