በምርጫ ተሳትፎ ዙሪያ በኢሕአፓ አባላት መካከል ተፈጥሮ የነበረው ውዝግብ በማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ መቋጨቱ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መሳተፉን በደገፉ እና በተቃወሙ አባላቱ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ውዝግብ በማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ መቋጨቱን ለአሐዱ ሬዲዮ ያስታወቁት የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ሚስጥረ-ሥላሴ ታምራት ናቸው።

ዋና ጸሐፊዋ በማብራሪያቸው፣ ፓርቲው ከሌሎች 4 ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሠረተው ትብብር በምርጫው ለመሳተፍ ቢስማማም ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ነበሩ ብለዋል።

ቅድመ ሁኔታዎቹም፡- በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶች ቆመው እውነተኛ ድርድር እንዲካሄድ እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የሚሉ ናቸው።

የተቀመጡት ጥያቄዎች ባለመሟላታቸው በምርጫው መሳተፍ የለብንም በሚሉና መሳተፍ አለብን ባሉ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ዋና ጸሐፊዋ አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ፤ ማዕከላዊ ኮሚቴው በምርጫው በመሳተፍ መታገል ይሻላል የሚል ውሳኔ በማሳለፉ ውዝግቡ መቋረጡን አብራርተዋል።

ፓርቲው ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታዎች መንግሥት በቸልተኝነት የሚያልፋቸው ከሆነ፣ ምንም እንኳን ምርጫው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄድ ቢሆንም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ፓርቲው የሚወስናቸው ሌሎች ፖለቲካዊ እርምጃዎችና ውሳኔዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ዋና ጸሐፊዋ ሚስጥረሥላሴ ታምራት ለአሐዱ ሬዲዮ ተናግረዋል።

#አሐዱ_


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: