በትምህርት ዘርፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚያሳድገው “ArifSchool” በይፋ ተዋወቀ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja: የሀገሪቱን የትምህርት ዘርፍ የእሴት ሰንሰለት በቴክኖሎጂ ለማቀናጀትና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ብሄራዊ ስትራቴጂን ግቦች ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀው “ArifSchool” የተሰኘ የተቀናጀ የዲጂታል ትምህርት ስነ-ምህዳር በዛሬዉ እለት ይፋ ተደርጓል።

በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ጥምረት በአራት ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂና የትምህርት ተቋማት ማለትም በአሪፍፔይ (Arifpay)፣ ኤአይቲ (AIT)፣ ገበያ (Gebeya – Dala Studios) እና ኤጁኬሽን ማተርስ (EducationMatters) መካከል የተመሰረተ ነው።

ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ የትምህርት ቤት አስተዳደርን፣ የፋይናንስ ግብይትን፣ በሰው ሰራሽ አስተዋፅዖ (AI) የታገዙ የመማሪያ መሳሪያዎችን እና የስነ-ምህዳር ምክር አገልግሎትን በአንድ ጥላ ስር የሚያገናኝ ስለመሆኑ ተገልጿል።

በማስተዋወቂያ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፣ እያንዳንዱ ተቋም በዘርፉ ያለውን ልምድና ቴክኖሎጂ አቀናጅቶ ያቀረበ ሲሆን የትምህርት ቤት ክፍያዎችን፣ የወላጆችን መዋጮ እና የሰራተኞችን ደሞዝ በዲጂታል መንገድ በማዘመን የትምህርት ቤቶችን የፋይናንስ አስተዳደር ሸክም እንደሚቀንስ የተገለፀ ሲሆን ይህም የሀገሪቱን የዲጂታል ክፍያ በ2030 ሰባት እጥፍ ለማሳደግ ከተቀመጠው ብሄራዊ ግብ ጋር የተናበበ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ብሄራዊ የትምህርት ደረጃን የጠበቀ የትምህርት ቤት ማኔጅመንት እና የኢ‐ለርኒንግ መድረክን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ይህም የተማሪዎችን ክትትል፣ የክፍል መርሃ-ግብር፣ ምዘና እና ምናባዊ ክፍሎች (Virtual Classrooms) በስርዓት ለመምራት ያስችላል፣ተማሪዎችና መምህራን የራሳቸውን የፈጠራ ስራዎች፣ የታሪክ መጽሃፍት፣ የዝግጅት ማቅረቢያዎች እና ድረ-ገጾች እንዲያዘጋጁ የሚያስችሉ የጄነሬቲቭ ኤአይ (Generative Al) ቴክኖሎጂዎችን የሚያበረክት መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪ የቴክኖሎጂውን ዘላቂነት ለማረጋገጥ የአቅም ግንባታ፣ የስልጠና ድጋፍ፣ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እና የለውጥ አመራር (Change Management) ስራዎችን እንደሚያከናውን ታውቋል።

ይህ ዘመናዊ መፍትሄ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር የሚከናወን ሲሆን፤ በገጠርም ሆነ በከተማ ለሚገኙ የመንግስት፣ የግል እና የህዝብ ትምህርት ቤቶች እኩል ተደራሽ እንዲሆን ተደርጎ መቅረጹ ተገልጿል።

በዛሬዉ እለት ይፋ በተደረገዉ አዲስ ቴክኖሎጂ አራቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራርመዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1