በኢትዮጵያ የእቃ አስተላላፊነት ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነ‼️
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ የእቃ አስተላላፊነት ዘርፍን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ ውሳኔ አስተላለፈ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ በትናንትናው ዕለት ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ የእቃ አስተላላፊነት ዘርፍን ለውጭ ባለሃብቶች ተሳትፎ ክፍት ለማድረግ ውሳኔ አሳልፏል።
ቀደም ሲል በደንብ ቁጥር 474/2012 የውጭ ባለሀብቶች የዕቃ አስተላላፊነት የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች የቅንጅት ኢንቨስትመንት የተከለለ ሲሆን የውጭ ባለሃብቶች የካፒታል የሽርክና ተሳትፎም በ49% ተገድቦ ቆይቷል።
ከዚህም የተነሳ በዘርፉ የሚፈለገውን አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ክፍተት ፈጥሮ የቆየ ሲሆን የቦርዱ ውሳኔም ይህን እና መሰል ችግሮችን የሚቀርፍ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በዘርፉ የተሰማሩ ነባር ባለሃብቶችንም ሆነ አዲስ ወደ ዘርፉ ለሚገቡት ባለሃብቶች በሎጂስትክስ ዘርፉ ላይ ተጨማሪ እምነት እንዲያሳድሩም የሚያግዝ ነው ተብሏል።
በውሳኔው መሰረት ዘርፉን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ማድረግ ፈጣን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት፣ አገራዊ የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት እንዲሁም የአገር ውስጥ ተዋናዮች አቅማቸውን አሳድገው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
@Seledadotio

No comments yet.