#Ethiopia | ተቋሙ በዚህ ገበያ ላይ መመዝገቡን ይፋ ያደረገው ከኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ጋር በመተባበር በሰጠው የጋራ መግለጫ ነው።
እስካሁን በሀገሪቱ የመጀመሪያውና ብቸኛው የተደራጀ የካፒታል ማርኬት የሆነው እና በመንግሥትና በግል አጋርነት የተመሠረተው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ላይ በይፋ ተመዝግበው ተሳታፊ የሆኑት ሦስት የፋይናንስ ተቋማት ብቻ ነበሩ።
መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ተቋም በሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ መድረክ ላይ ከመመዝገቡ አስቀድሞ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖቹን ለሽያጭ ገበያ አውጥቶ ነበር።
ኩባንያው ባለፈው ሚያዝያ ወር ባወጣው መግለጫ ለአራት ወራት ያህል ክፍት ሆኖ በቆየው በዚህ የሽያጭ ሂደት ለሽያጭ ካቀረበው የ10 በመቶ የኩባንያው ድርሻ ውስጥ 10.7 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ብቻ የተሸጡ ሲሆን፤ቀሪዎቹ 89.3 ሚሊዮን አክሲዮኖች ግን ሳይሸጡ ቀርተዋል።
በተመሳሳይ ተቋሙ ከአክሲዮን ሽያጩ 30 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም ማሳካት የቻለው ግን 3.2 ቢሊዮን ብር ብቻ እንደሆነ መግለጹ አይዘነጋም።
በዚህ የሽያጭ ሂደት ላይ ከ47 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አክሲዮን መግዛታቸውን ተቋሙ አስታውቋል።
አክሲዮን ከገዙ ዜጎች ውስጥ 45,336 የሚሆኑት “የባለቤትነት ማረጋገጫ” እና “አክሲዮኖችን ወደ ዲጂታል የመቀየር ሂደታቸውን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቃቸው በዛሬው መርሃ ግብር ላይ ተገልጿል።
የባለቤትነት ማረጋገጫ ሂደታቸውን ያጠናቀቁ ዜጎች አክሲዮኖች በገንዘብ ሲሰላ 3.04 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው መሆናቸውንም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
አክሲዮን ከገዙ ባለሀብቶች ውስጥ 3.7 በመቶ የሚሆኑት የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ባለማቅረባቸው እና ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌላቸው በመሆኑ፤ ለአክሲዮን ግዢ የከፈሉት ገንዘብ ተመላሽ እንደሚደረግላቸው የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ በዛሬው መርሃ ግብር ላይ ተናግረዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ



Source: GetuTemesgen









No comments yet.