ግንቦት 21 ከቃጥላ አይቀርም!

- Advertisement -
Sidebar AD

ለቃል መውረድ ለሥጋ ማረግ ምክንያት የሆነችው የእመቤታችን በአለ ንግስ በቃጥላ!

እንኳን ለደብረ ምጥማቅ በዓል አደረሳችሁ!

በደብረ ምጥማቅ ከግንቦት 21-25 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብርሃን ተጎናጽፋና በሠራዊተ መላእክት ታጅባ ተገልጣለች፤ በዚያን ጊዜም ሱራፌል ማዕጠንታቸውን ይዘው ሰገዱላት፤ እንዲህ እያሉም አመሰገኗት፤ ‹‹አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ ያለ አላገኘም፤ ባንቺም ሰው ሆነ፡፡››(መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰)

የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳውያን ግንቦት 21 የደብረ ምጥማቅን በዓል በቃጥላ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም በማሳለፍ ከበረከቷ ተካፋይ እንድትሆኑ በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጋብዛችኋል፡፡

እመቤታችን የህይዎታቸውን ቋጠሮ የፈታችላቸው በእንባ ሲመሰክሩ ያያሉ። ይምጡ ፣ ጌታም ሸክማችሁ የከበዳችሁ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ እንዳለ።

የቤተክርሲያኒቱን የልማት ሥራዎች ለመደገፍ፡-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000249446975
አባይ ባንክ አካውንት አካውንት ቁጥር 1641119233527011


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: