ሙዝደሊፋ በሚና እና በአረፋት መካከል የሚገኝ ሲሆን የአረህማን እንግዶች ከአረፋ ተመልሰው ሌሊቱን የሚያሳልፉበት ቦታ ነው።
ከመላው ዓለም የመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማኞች የቆዳ ቀለም፣ የሀብት ደረጃ፣ ዜግነት እና የስልጣን ተዋረድ ሳይለያቸው ለፈጣሪያቸው ክብር እኩል ሜዳ ላይ ጎን ለጎን የሚያርፋበት ልዩ ቦታ ነው።
ይህ ጣሪያና ግድግዳ አልያም ምንጣፍ የሌለው አቧራማ ሜዳ የሰው ልጆች ሁሉ በአላህ ፊት እኩል መሆናቸውን የሚመሰክር ታምራዊ ቦታ ነው።
ሙዝደሊፋ የመላው ዓለም ሙስሊሞች እኩልነታቸውንና አንድነታቸውን የሚያሳዩበት እንዲሁም የቀብር ዓለምን የሚያስታውሰበት ስፍራ ነው።
Via: የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት



Source: FastMereja









No comments yet.