የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ የመስጠት መብት ለሁሉም የሀገሪቱ የንግድ ባንኮች መፍቀዱ

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ የመስጠት መብት ለሁሉም የሀገሪቱ የንግድ ባንኮች መፍቀዱን አስታወቀ

#Ethiopia | ​ቀደም ሲል ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ (Export Permit) የመስጠት ስልጣን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረው አሰራር ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል።

​ማዕከላዊ ባንኩ ይህንን እርምጃ የወሰደው በወጪ ንግድ ላይ ያሉ ቢሮክራሲዎችን ለማቃለል፣ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለመጨመር እና ለላኪዎች ምቹና ፈጣን የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ነው።

​ሁሉም ፈቃድ ያላቸው የንግድ ባንኮች ከዛሬ ጀምሮ ከተለመዱት የወጪ ንግድና የውጭ ምንዛሬ መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ አገልግሎቱን ለደንበኞቻቸው መስጠት እንዲጀምሩ በጥብቅ ታዟል።

ይህ አዲስ መመሪያ ላኪዎች የመረጡት ባንክ ዘንድ ሄደው ጉዳያቸውን እንዲያስፈጽሙ በር የሚከፍት በመሆኑ፣ የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ በእጅጉ ያነቃቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#የኢትዮጵያብሔራዊባንክ #የወጪንግድ #ቻይና #ኢትዮጵያ #ባንክ #ቢዝነስ #EthiopianEconomy #NBE


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1