ቀኝ አዝማች በኩረ ምዕመናን ትዛዙ ኮሬ የኢትዮጵያን ባህል፣ ቱሪዝምና በጎ አድራጎት በማስፋፋት የሚታወቁ ታዋቂ ኢንተርፕረነር፣

- Advertisement -
Sidebar AD

ቀኝ አዝማች በኩረ ምዕመናን ትዛዙ ኮሬ የኢትዮጵያን ባህል፣ ቱሪዝምና በጎ አድራጎት በማስፋፋት የሚታወቁ ታዋቂ ኢንተርፕረነር፣ የባህል አምባሳደር እና ሀገር በቀል ሽማግሌ ናቸው። በተለይም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን እና ግዙፍ የባህል ምግብ ቤቶች አንዱ የሆነውን ዮድ አቢሲኒያ (Yod Abyssinia) ባህላዊ ምግብ ቤት በመመስረታቸው በሰፊው ይታወቃሉ።

ስለ ቀኝ አዝማች ትዛዙ ኮሬ ዋና ዋና መረጃዎች
የዮድ አቢሲኒያ መስራችና ባለቤት በ1996 ዓ.ም.
(እ.ኤ.አ. በ2003) ዮድ አቢሲኒያ ባህላዊ ምግብ ቤትን መስርተዋል።
ምግብ ቤቱ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ምግቦች፣ ሙዚቃዎች እና ውዝዋዜዎች ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ዜጎች በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና አለው።
እንደ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ያሉ በርካታ የዓለም መሪዎችን እና የውጭ አገር ዲፕሎማቶችን በምግብ ቤታቸው አስተናግደዋል።

❸ማኅበራዊ አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች

ማኅበራዊ አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች
ለተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት እና ችግረኛ ወገኖች ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ይታወቃሉ።
በበጎ አድራጎት ሥራዎቻቸው ምክንያት በ2016 ዓ.ም የፊላንትሮፒ (የበጎ አድራጎት) ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።
በማኅበረሰቡ ውስጥ ሰላምን ለማስፈንና እርቅ ለማውረድ እንደ ትልቅ የሀገር ሽማግሌ ሆነው ያገለግላሉ።

በጎ ተግባራት እና ማህበራዊ ሀላፊነት በመወጣት አርዓያነት ያለዉን ተግባራት በመስራት ይታወቃል።

የዓመቱን 360 ቀናት ለኢትዮጵያ ሀገራቸዉ እንዲሁም 4 ቀናት ለበጎ አድራጎት ተግባራት ሲውል ፤ 365 ኛውን ቀን ደግሞ ዕድገት እንደሚያስተዋዉቅ የሚያምኑት የድርጅቱ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ቀኝ አዝማች ትዛዙ ኮሬ ናቸዉ።
የዮድ አቢሲኒያ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ቀኝ አዝማች ትዛዙ ኮሬ እንዲሁም ድርጅታቸዉ ‘ዮድ አቢሲኒያ’ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር፣ ለሜሪጆይ ኢትዮጵያ ፣ ለቶራ የህፃናት ማሳደጊያ ፣ ለሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ፣ ለየወደቁትን እናንሳ የአረጋውያን መርጃ ማህበር ለሌሎችም በማገዝና በመርዳት ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት በጎ ስምና አርዓያነትን በተግባር ለማሳየት ችሏል።ወደፊትም ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

❹እዉቅናና ሽልማት

➢የዓመቱ በጎ ሰዉ ሽልማትና እዉቅና

ጳጉሜ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ለ12ኛ ጊዜ በተካሄደዉ የዓመቱ በጎ ሰዉ ሽልማትና እዉቅና በቅርስ ባህል እና ቱሪዝም ዘርፍ ዮድ አቢሲኒያ፡የባሕል ምግብ አዳራሽ ተሸልሟል።

የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦችን ፤ ውዝዋዜዎችን እና ባህላዊ እሴቶችን ለቱሪስቶች እና ማህበረሰቡ የሚያቀርብ ተቋም ሲሆን የኢትዮጵያን እሴቶችን በማስተዋወቅ ረገድ ያስቀመጠው ደማቅ አሻራ ከፍ ያለ ነዉ።

ዮድ አቢሲኒያ ባህል ባንድ
ለቱሪስቶች የአገራችንን ብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃዎች ዉዝዋዜን በማሳየት ቱባ ባህላችንን ሳይበረዝና ሳይከለስ ያሳያል።

➢ የቱሪዝም አዋርድ

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሐምሌ 6/2016ዓ.ም በአድዋ መታሰብያ ሙዚየም ባካሄደው የኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ምስረታና 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለከተማችን የቱሪዝም ልማትና እድገት የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቱሪዝም ተቋማትና አካላት የቱሪዝም አዋርድ ከተሰጡት መካከል አንዱ ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ ነዉ።

የቱሪዝም ተቋማቱ በሚሰጡት የአገልግሎት ጥራት ባላቸው የቱሪዝም ፈጠራ ስራ እንዲሁም የቱሪስት አያያዝና የመሳሰሉት መስፈርቶችን መነሻ በማድረግ ከዘርፉ 1ኛ በመዉጣት ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ፣የቱሪዝም አዋርድ ተሸልሟል።

➢”የ8ኛዉ የአርአያ ሰው ሽልማት”

ተቀማጭነቱን በሀገረ አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ያደረገው ዓድዋ የባህልና የታሪክ ኅብረት ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በዋናነትም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን አርአያ የሚሆን ሥራ ለሚሠሩ ግለሰቦችና ተቋማት”የአርአያ ሰው ሽልማት” በሚል ዕውቅና ይሰጣል፡፡

ለ8ኛ ግዜ በአዲስ አበባ ዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ ለሀገር ባለውለታዎች በተለይም በባህል ልማት፣ በተፈጥሮ ጥበቃ፣ በቱሪዝም እና ቅርስ እንዲሁም በታሪክ መስኮች ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማት ከተሰጣቸው መካከል ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ አንዱ ነዉ።

ዓለም አቀፍ እውቅና
የኢትዮጵያን ባህልና ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቃቸው “የባህልና ቱሪዝም አምባሳደር” የሚል ክብር ተሰጥቷቸዋል።
በቅርቡ (እ.ኤ.አ በ2025) በአሜሪካ ሲያትል በተካሄደው የ42ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል (ESFNA) ላይ ለሀገራቸው ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ ልዩ የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

❺ዋና ዋና ቅርንጫፎችና አድራሻዎች
ዮድ አቢሲኒያ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቁልፍ ቦታዎች ቅርንጫፎችን ከፍቶ ይገኛል፦
ቦሌ ቅርንጫፍ (ዋናው)፦ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ፣ ከብራስ ሆስፒታል ከፍ ብሎ የሚገኝ የነበረ ሲሆን አሁን ቀድሞ ከነበረበት በ100 ሜትር ገባ ብሎ ኬኬር ህንፃ አጠገብ ይገኛል።ለቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅርብ በመሆኑ ለቱሪስቶች ተመራጭ ነው።
ፒያሳ (ቴዎድሮስ አደባባይ) ቅርንጫፍ፦ በቅርቡ በዲል ፕላዛ ፊት ለፊት የተከፈተ አዲስና ዘመናዊ የባህል አዳራሽ፣ የስፖርት ባር (Sport Bar) እና የባዛር ማዕከል ነው።

ዮድ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል ሆቴል፦ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ ከፍ ብሎ፣ ወደ ወሰን በሚወስደው መንገድ ማዕድን ሚኒስቴር አጠገብ የሚገኝ ዘመናዊ ሆቴል ነው።

❻የ”ዮድ” መሪ ቃል በተግባር

የድርጅቱ መሪ ቃል የሃገራችን ኢትዮጵያን ”ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ ” የሚል ነው ባለፉት 22 ዓመታት የኢትዮጵያን ባህልና መስተንግዶን ጨምሮ ሲያስተዋውቅ ኖሯል ፡፡ ለዚህም አስተዋፅኦው ”የኢትዮጵያ የባህልና የቱሪዝም አምባሳደር” የሚል ዕውቅና ከመንግስት ተሰጥቶታል ፡፡

“ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ” በሚል መርህ ከመላው ዓለም ወደ ሃገራችን ለመጡ እንግዶች የባህል ምግብና መጠጦች መስተንግዶ በመስጠት ፣ የብሔር ብሄረሰቦችን ሙዚቃዎችና ውዝዋዜዎች በማቅረብ ፣ የሀገራችንን የታሪክ የባህልና የቱሪዝም ሃብቶችና ቅርሶቻችንን በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ በመገንባት ብዙ በመስራት ”የኢትዮጵያ የባህል እና የቱሪዝም አምባሳደር” የሚል እውቅናን ለማግኘት ችሏል፡፡

“ዮድ”
ዮድ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ
በእግዚአብሔር ቀኝ ያለ እሱ ኃያልና
ጽኑዕ የሆነ ነው ማለት በሌላ መልኩ”ዮድ” ማለት በጉራጌ ቋንቋ “መመስከር ወይም መናገር” ማለት ነዉ።

ከ1996ዓ.ምማለትምላለፉት 22 ዓመታት በተለያዩ ወቅቶች ወደ ሀገራችን የመጡ በርካታ የሀገራት መሪዎችን ፣ ዲፕሎማቶችን ፣ የዓለም ታላላቅ ሰዎችን፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ ታዋቂ ሰዎች ፣ ባለሀብቶች ፣ አትሌቶች ፣ አርቲስቶች የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎችም በሺዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶችንና ኢትዮጵያዊያን እንግዶችን ተቀብሎ በፍቅርና በአክብሮት ሲያስተናግድ የቆየው ዮድ አቢሲኒያ በቀጣይም በሀገራችን ለሚከናወኑ ታላላቅ ሁነቶች ሙሉ አገልግሎት ለመስጠት ከወትሮው በተለዬ አኳኋን መዘጋጀቱ ተስተዉሏል።በ500 ብር ካፒታል እና በአነስተኛ የስራ ጅምር በጥረት የተገነባ ካምፓኒ በበርካታ ፈተናዎች ዉስጥ አልፎ ዛሬ በርካታ ቁጥር ላላቸዉ ወገኖቻችን የስራ ዕድል መፍጠር የቻለ ግዙፍ ኩባንያ ለመሆን በቅቷል።

“የሃገራችን ኢትዮጵያን ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ ”ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ

ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሲሳይ መንግስቴ






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1