የነገሌ ቦረና አባ ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በይፋ ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻ የሆነውን አዲሱን የነገሌ ቦረና አባ ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን በዛሬው ዕለት በይፋ መርቀዋል። እንደ ቦይንግ 737 ማክስ ያሉ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ማስተናገድ የሚችለው ይህ ማረፊያ፣ የአካባቢውን የንግድ፣ የቱሪዝምና ድንበር ተሻጋሪ ትስስርን ለማሳደግ ታቅዶ የተገነባ ሲሆን በሳምንት ሦስት ቀናት መደበኛ በረራዎችን እንደሚያስተናግድ ታውቋል።

​የአውሮፕላን ማረፊያውን መመረቅ አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሚገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ከመፍጠሩም በላይ የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ አቅም እንደሚያነቃቃና ሕዝብን ይበልጥ እንደሚያቀራርብ ገልጸዋል። አያይዘውም 80ኛ ዓመቱን የያዘውና የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” መሆኑን በተግባር እያሳየ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: