ተለያይቻለሁ !!!

- Advertisement -
Sidebar AD

ውድ ወዳጆቼ…
ከዛሬ ዘጠኝ ወራት በፊት ከቻናል ዋን የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር የጣቢያው “Creative Director” በመሆን የሥራ ውል ማሰሬንና ሥራ መጀመሬን በማህበራዊ ሚዲያ መግለጼ ይታወሳል።
ሥራ ከጀመርኩበት ቅጽበት ጀምሮ ጣቢያው የቅዳሜ ሾው ያልነበረው በመሆኑ “ቅዳሜኛ” የተሰኘ የመዝናኛና መረጃ (Magazine Format Infotainment Weekly Show) ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ በመፍጠርና በማዘጋጀት ላለፉት 6 ወራት በአየር ላይ ቆይቷል። በአጭር ጊዜም ከተመልካቾች ዘንድ እውቅናና ተወዳጅነት ማግኘት ችሏል።
“ቅዳሜኛ” የ3 ሰዓት ቆይታ ያለው ሲሆን በዚህ ቆይታው ውስጥ “ቁራሌው”፣ “ከመወሰንዎ በፊት”፣ “ወጌሻ”፣ “ቢሆንስ”፣ “ቻሌንጅ አንድ”፣ “ሸርሸር”፣ “ለማጅ”፣ “ጨዋታ አንድ”፣ “በላተኞቹ” እና “አቃቂር” የተሰኙ አስተማሪና አዝናኝ ይዘቶችን በመፍጠርና በማዘጋጀት ሰርቻለሁ። እንዲሁም በበዓላት ወቅት የተላለፉ የበዓል ሪያሊቲ ሾዎችንም በመፍጠርና በማዘጋጀት ተሳትፌያለሁ።
ከዚህ በተጨማሪም ለሜንስትሪም ሚዲያው አዲስ የሆኑ ነገር ግን ተሰጥኦ ያላቸው ፕሮግራም አቅራቢዎች አቅማቸውን እንዲያወጡ እድል ከመስጠት ባለፈ፣ ሙያው የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር ተከትለው በኃላፊነት እንዲሠሩ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ሞክሬያለሁ።
ሲቀጥል…
አሁን ከዘጠኝ ወራት ቆይታ በኋላ ከጣቢያው ጋር የነበረኝን ውል ማቋረጤን እየገለጽኩ፣ በነበረን የሥራ ጊዜ በትጋትና በመረዳዳት አብረውኝ ለነበሩ የ“ቅዳሜኛ” ሾው አባላት፣ የተቋሙ ካሜራማኖችና ኤዲተሮች ላሳያችሁኝ አክብሮትና ቀናነት ከልብ እያመሰገንኩ ወደፊትም መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
እንዲሁም በጣቢያው ላይ ይተላለፉ የነበሩ ፕሮግራሞችን በመከታተል በተለያየ መንገድ ጠቃሚ አስተያየቶችን ትሰጡኝ የነበራችሁ ወዳጆቼንም በተለይ ማመስገን እወዳለሁ።
አክባሪያችሁ
ሳምሶን ከበደ
Film writer & director | producer|creative director | host




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: