ለክቡራን የሥራ አጋሮቼ፤ ወዳጆቼ በሙሉ፣
#Ethiopia | ከዘጠኝ ወራት በፊት ከቻናል ዋን የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በፈጠራ ዳይሬክተርነት (Creative Director) ለመሥራት ተስማምቼ ወደ ሥራ መግባቴን በዚህ ገጼ ማጋራቴ ይታወሳል።
ወደ ተቋሙ ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን ክፍተት በመሙላት፣ ጣቢያው ቀደም ሲል ያልነበረውን የቅዳሜ መዝናኛ ፕሮግራም አዲስ መልክ አስይዤ ለመቅረጽ ተንቀሳቅሻለሁ።
በዚህም መሠረት መረጃና መዝናኛን ያቀናጀውን የቅዳሜኛ ሳምንታዊ ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ በመቅረጽና በማዘጋጀት ላለፉት ስድስት ወራት በአየር ላይ እንዲቆይ አድርጌያለሁ። ፕሮግራሙም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰፊ የተመልካች ድጋፍና ተወዳጅነትን ማትረፍ ችሏል።
በየሳምንቱ ለሦስት ሰዓታት በሚተላለፈው በዚህ ፕሮግራም ውስጥ እንደ ቁራሌው፣ ከመወሰንዎ በፊት፣ ወጌሻ፣ ቢሆንስ፣ ቻሌንጅ አንድ፣ ሸርሸር፣ ለማጅ፣ ጨዋታ አንድ፣ በላተኞቹ እና አቃቂር ያሉ አዝናኝና አስተማሪ ዓምዶችን በመፍጠር ሰርቻለሁ።
ከነዚህም በተጨማሪ በበዓላት ወቅት ለአየር የበቁ ልዩ ልዩ የሪአሊቲ ሾው ፕሮግራሞችን በማዘጋጀትና በማስተባበር ተሳትፎ አድርጌያለሁ።
ከይዘት ዝግጅቱ ባለፈ፣ ለቴሌቪዥን ሚዲያ አዲስ የሆኑ ነገር ግን ከፍተኛ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች ብቃታቸውን የሚያሳዩበትን ዕድል አመቻችቻለሁ።
እነዚህ አቅራቢዎች የሙያውን ሥነ ምግባር ጠብቀው በኃላፊነት ስሜት እንዲሠሩም የበኩሌን የሙያ ድጋፍና ክትትል አድርጌላቸዋለሁ።
አሁን ግን ከዘጠኝ ወራት የሥራ ቆይታ በኋላ ከጣቢያው ጋር የነበረኝን የሥራ ውል ማቋረጤን ለመግለጽ እወዳለሁ። በነበረን ቆይታ በትጋትና በጋራ ስሜት አብረውኝ ለሠሩት የቅዳሜኛ ፕሮግራም አባላት፣ ለካሜራ ባለሙያዎችና ለኤዲተሮች ላሳዩኝ ወንድማዊ አክብሮትና ቀናነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ለወደፊቱም መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
በመጨረሻም፣ በጣቢያው ላይ የሚተላለፉ ሥራዎቼን በመከታተል ገንቢና ጠቃሚ አስተያየቶችን ስትለግሱኝ ለነበራችሁ ውድ ተመልካቾቼና ወዳጆቼ ሁልጊዜም ከፍ ያለ ምስጋና አለኝ።
አክባሪያችሁ፣
ሳምሶን ከበደ
የፊልም ደራሲ፣ ዳይሬክተር፣ ፕሮዲውሰር እና አቅራቢ
#channelone #samsonkebede #kedamegna #media #tvshow #entertainment #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.