የሰዓሊ መሐሪ ተሾመ አዲስ የሥዕል አውደ ርዕይ በስውር መልክ በሚል ርዕስ መቅረብ ጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኪነ ጥበብ አፍቃሪዎች ዘንድ ከፍተኛ አክብሮትና እውቅና ያገኘው ሰዓሊ መሐሪ ተሾመ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎቹን ለአንባቢና ለተመልካች ያቀረበበትን ልዩ የሥዕል አውደ ርዕይ ለሕዝብ ክፍት አድርጓል።

ሥነ ጥበብ ለሀገር ዕድገትና ለኅብረተሰብ ንቃተ ሕሊና ያለው ጠቀሜታ በቀላሉ የሚገመት አይደለም። የሰዎች የዕለት ተዕለት ሕይወት እንቅስቃሴ፣ የምንገለገልባቸው ቁሳቁሶች ቅርፅ፣ የሕንጻዎች ውበት፣ አልባሳት፣ የአካባቢ ጥበቃ ገጽታና የገንዘብ ኖቶች ሳይቀሩ ከዲዛይን ጥበብ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አላቸው።

ዲዛይን ደግሞ የሥዕል ጥበብ ዋና አካል በመሆኑ ጥበብ በሰዎች ሕይወት ላይ የላቀ ተፅዕኖ የማሳደርና የሀገር መገለጫ የመሆን አቅም አለው።

ይህ አውደ ርዕይ እየተስተናገደበት የሚገኘው አርታዊ ጋለሪ ከተመሠረተ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ በርካታ የሥዕልና የፎቶግራፍ ሥራዎችን ለዕይታ በማብቃት ረገድ ስኬታማ ሆኗል።

ጋለሪው ባለሙያዎችን ከማኅበረሰቡ ጋር በማገናኘትና የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት በኩልም ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

ስውር መልክ ወይም ዘ ሂድን ፎርም በተሰኘ መሪ ቃል የተዘጋጀው የዚህ ልዩ አውደ ርዕይ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ግንቦት 15 ቀን የተከናወነ ሲሆን ኤግዚቢሽኑ እስከ ሰኔ 7 ቀን ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

የሥዕል ማሳያ ቦታው በቦሌ ብራስ ኬኬር ሆቴል ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ይገኛል። የጥበብ ወዳጆችና የሥዕል አፍቃሪዎች በቦታው በመገኘት በቅርፅና በቀለም የተቃኙትን የሰዓሊውን ድንቅ የፈጠራ ሥራዎች እንዲመለከቱና የኪነ ጥበቡ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ ተላልፏል።

#art #painting #exhibition #artgallery #culture #fineart #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2