#Ethiopia | የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን አስመልክቶ የእስልምና እምነት ተከታዮች በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሶላት ስነ- ስርዓት አካሂደዋል።
የኃይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች፣ የውጭ ሀገር ዜጎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተካሄደው የሶላት ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡
የሶላት ስነ-ስርዓቱ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም ተብሎ ለተሽከርካሪ ዝግ የነበሩ መንገዶቸ መከፈታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ለፕሮግራሙ ስኬታማነት አስተዋፆኦ ላደረጉ አካላት፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች እና አባላት ዋና ጠቅላይ መምሪያው ምስጋናውን በማቅረብ ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የሠላም እና የደስታ እንዲሆንም መልካም ምኞቱን ገልጿል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.