ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋስይሁን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በፌስቡክ ገጹ “እናቴ ሰላምዬ ጠፋችብኝ፣ ሞተችብኝ” በሚል ያሰራጨውን መረጃ ተከትሎ፣ እውነታውን ለማስረዳት እናቱ እትዬ ሰላማዊት ጥሩ እና ታላቅ እህቱ ፍቅርተ ዋስይሁን በሸገር ኢንፎ ስቱዲዮ ተገኝተዋል።
እናቱ እትዬ ሰላም በህይወት መኖራቸውን እና ጋዜጠኛ ሶፎንያስ በአሁኑ ሰዓት ያለበትን እጅግ አሳሳቢ የጤና ሁኔታ አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ፦
ሶፎንያስ እናቴ ጠፋችብኝ ቢልም፣ እናቱ ግን ከልጃቸው የአእምሮ መታወክ እና ሊሰነዝርባቸው ከነበረው ጥቃት ራሳቸውን ለማዳን ሲሉ ብቻ ከቤት ሸሽተው መውጣታቸውን በቪዲዮው ያረጋግጣሉ።
ከዚህ ቀደም የነበረበት የአእምሮ ህመም አገርሽቶበት ከህክምና ተቋም ካመለጠ በኋላ፣ በገዳም ቆይታው መድሃኒት በማቋረጡ ምክንያት ሁኔታው ይበልጥ ውስብስብና ከአቅም በላይ ሊሆን ችሏል።
በመኖሪያ ቤት የደረሰው አደጋ፦ ከቀናት በፊት በቤቱ ውስጥ በሩን ቆልፎ ንብረት ያወደመ ሲሆን፣ የቤት አስቤዛዎችን በመድፋት እና ዘይት በማንተክተክ “የቀረበኝን ሰው እገላለሁ” በማለቱ ፖሊሶች መስኮት ሰብረው በመግባት ሊቆጣጠሩት እንደቻሉ ተገልጿል።
የኔ ቤተሰብ ሳይቀር በእሱ ምክንያት አግለውኛል የሚሉት የሶፎንያስ እናት ልጃቸውን የትዳር እና የልጅ ባለቤት ሆኖ ለማየት እንጂ እንዲህ አይነቱ ፈተና ላይ ይወድቃል ብለው እንዳልጠበቁ ገልጸው፣ ሶፎንያስን ብቻዋን በብዙ መከራ (ሊስትሮ ጠርጎ እና ፓርኪንግ ሰርቶ) ለቁም ነገር ያበቃችው እናት በመሆኗ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጇን ከዚህ የከፋ ህመም እንዲታደግላት በሸገር ኢንፎ በዕንባ ትማጸናለች።



Source: FastMereja







No comments yet.