የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በድሬደዋ ባለ 10 ፎቅ ሁለገብ የንግድ ማዕከል ግንባታ መጀመሩን አስታወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ በድሬደዋ ከተማ አዲስ የልማት ፕሮጀክት በይፋ አስጀምሯል።

ኮርፖሬሽኑ በከተማዋ ኢሚግሬሽን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚያስገነባው ይህ ዘመናዊ ሁለገብ የንግድ ሞል ባለ 10 ወለል ሲሆን፣ በርካታ የንግድ ሱቆችንና ደረጃቸውን የጠበቁ የቢሮ ክፍሎችን ያካተተ ነው።

በተያያዥም የከተማዋን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማነቃቃት የሚረዱ ተጨማሪ 13 የንግድና የመኖሪያ ሕንፃዎችን ለመገንባት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ለእነዚህ አዳዲስ ግንባታዎች የሚሆኑ የ13 ፕሮጀክት ቦታዎች የአዋጭነት ጥናት በአሁኑ ወቅት በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ በበዓሉ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ተገልጿል።

ኮርፖሬሽኑ ይህንን ሰፊ የጥናት ሥራ ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምረት እያከናወነው ሲሆን፣ ግንባታዎቹ ተጠናቀው ለአገልግሎት ሲበቁ ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገትና የገጽታ ለውጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል።

ይህ የኮርፖሬሽኑ የወርቅ ኢዮቤልዩ የምስረታ በዓል ከግንቦት 10 እስከ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተለያዩ ማህበረሰባዊና ተቋማዊ ዝግጅቶችን በማካተት በድሬደዋ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ሲከበር ሰንብቷል።

#ድሬደዋ #የፌዴራልቤቶችኮርፖሬሽን #የንግድሞል #ልማት #ከተማግንባታ #DireDawa #FederalHousingCorporation #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1