ብሔራዊ ባንክ በቁጠባና ብድር ማኅበራት ላይ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሊጀምር መሆኑ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ይታደጋል ተባለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቁጠባና ብድር ማኅበራትን በቀጥታ ለመቆጣጠር የወሰነው እርምጃ፣ ዘርፉ ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር መሸሸጊያ እንዳይሆን ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር የፋይናንስ ባለሙያ ገለጹ።
ባለሙያው አቶ ገመቹ ብርሃኑ፤ ማኅበራቱ ከብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ውጪ መቆየታቸው በፋይናንስ ገበያው ላይ ከፍተኛ መዛባትና የደህንነት ስጋት ደቅነው መቆየታቸውን ለጣቢያችን ጠቁመዋል።
የፋይናንስ ባለሙያው አቶ ገመቹ ብርሃኑ እንደገለጹት፤ እስካሁን ማኅበራቱ የብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር ማዕቀፍ ውስጥ አለመኖራቸው ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወይም “መኒ ላውንድሪንግ”ሰፊ በር ከፍቶ ቆይቷል።
ሕገ-ወጥ ገንዘብ ያላቸው አካላት የገንዘቡን ምንጭ ለመደበቅ በአባላት ቁጠባ ስም በትናንሹ እየከፋፈሉ ወደ ማኅበራቱ በማስገባት፣ ወደ ሕጋዊ የባንክ ሥርዓት እንዲቀላቀል ሲያደርጉት መቆየታቸውን ባለሙያው ጠቁመዋል።
አዲሱ አሰራር ግን ይህንን የገንዘብ ማጠብ ሥራ ለመቆጣጠር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል።
ባለሙያው አክለውም፣ ማኅበራቱ እንደ ባንኮች ጥብቅ የካፒታልና የሥራ ማስኬጃ መመሪያዎች የማይገዟቸው መሆኑ በገበያው ላይ ያልተመጣጠነ ውድድር ሲፈጥሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
በተለይም አንዳንዶቹ ማኅበራት እስከ 30 በመቶ ወለድ እንከፍላለን በማለት የተጋነነ ዋጋ ለብር ሲሰጡ መቆየታቸው በገበያ ላይ የተለያየ የብር ዋጋ እንዲፈጠርና ለገበያ አለመረጋጋት ዋነኛ መንስኤ መሆኑን አቶ ገመቹ አስረድተዋል።
እንደ አቶ ገመቹ ገለጻ፤ አዲሱ መመሪያ ትናንሽ ማኅበራትን ከገበያ ያወጣቸዋል የሚል ሥጋት ቢኖርም፣ ይልቁንም ትላልቆቹ ወደ ማይክሮ ፋይናንስነት እንዲያድጉ ሊያበረታታቸው ይችላል።
አሰራሩ ጥቂት ባለሀብቶች በማኅበራቱ ውስጥ ያላቸውን ተጽዕኖ በመቀነስ፣ ተራው ቆጣቢ ዜጋ ያከማቸው ገንዘብ በተሻለ ሁኔታ እንዲጠበቅለትና ዋስትና እንዲያገኝ የሚረዳ መሆኑንም ባለሙያው አክለዋል።
ይህ የብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር እርምጃ በሀገሪቱ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠርና የኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማምጣት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ሲሉ የፋይናንስ ባለሙያው አቶ ገመቹ ብርሃኑ አስረድተዋል።
ልዑል ወልዴ
@Seledadotio

No comments yet.