#Ethiopia | ቴክኖ ኢትዮጵያ ለፈጠራ እና ለሥነ ጥበብ ባለሙያዎች አዲስና ማራኪ የትብብር ዕድል ይዞ ቀርቧል።
ተቋሙ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ከቦርድ ሴልፎን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በቴክኖ ካሞን ስልክ የተቀረጹ ምስሎችን በፎቶ ኤግዚቢሽን አማካኝነት ለታዳሚዎች ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።
በዘንድሮው ዓመት ደግሞ አዲስ በሚያስተዋውቀው የካሞን 50 ሲሪየስ ስልክ ሞዴል አማካኝነት ይበልጥ ደመቅ ያለና ሰፊ የፎቶ ኤግዚቢሽን ለማዘጋጀት ያቀደ ሲሆን ለዚህም ስኬት ከተለያዩ የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በጋራ ለመሥራት ፍላጎት አለው።
ይህን ከቴክኖ ሞባይል ጋር አብሮ የመሥራት መልካም ዕድል መጠቀም ለምትፈልጉ ማናቸውም የኢንስታሌሽን አርት፣ የኪነ ሕንጻ ግድግዳ ሥዕል (ሙራሊስት)፣ የቅርጻ ቅርጽ፣ የሴት ዲዛይን፣ የፋሽንና ጨርቃጨርቅ፣ የዲጂታል አርት፣ የሞሽን ግራፊክስ፣ የባሕላዊ እደ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለምትሰሩ የፈጠራ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ጥሪው ቀርቧል።
ከታች የተያያዘውን የቅጽ ማስፈንጠሪያ በመጫን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ማግኘትና በዕድሉ ለመሳተፍ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን መልካም ዕድል እንመኛለን።
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfOovbbXJbCPpibYdioFSjaXsSIP2TKKachBcCPaVErrQYfsQ/viewform?usp=publish-editor
#TecnoEthiopia #Camon50 #ArtExhibition #CreativeArts #EthiopianArtists #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.