ኢ/ር ታከለ ኡማ በትውልድ ቦታው ዘመናዊ ትምህርት ቤት አስገነባ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ ጎሮሶሌ ከተማ፣ በዓይነቱ ለየት ያለና ዘመናዊ የሆነ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከተለያዩ ድርጅቶች ገንዘብ በማሰባሰብ በማስገንባት ለአገልግሎት መዘጋጀቱ ተገለፀ።

ይህ “በረዋቅ” የተሰኘው ትምህርት ቤት የቀድሞው ማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተለያዩ ተቋማትን በማስተባበር ያስገነቡት መሆኑ ታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው ይህ አዲስ የትምህርት ተቋም፣ በሀገሪቱ ካሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች በተለየ መልኩ እጅግ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟላ መሆኑ ተመልክቷል።

ትምህርት ቤቱ የውስጥና የውጪ ውበቱን የጠበቀ ከመሆኑም በላይ፣ ለአስተማሪዎች መኖሪያ ቤት፣ ዘመናዊ ቤተ-መጻሕፍት (Smart Libraries)፣ የላቦራቶሪ ክፍሎች፣ እንዲሁም የእግር ኳስና የቅርጫት ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን ያካተተ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በትምህርት ክፍሎቹ ውስጥ የኤልኢዲ (LED) ስክሪኖች የተገጠሙላቸው ሲሆን፣ ይህም በርቀት (Virtually) ጭምር ለማስተማር የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

የአንድ ክፍል የተማሪዎች ቁጥርም የትምህርት ጥራትን ለመጠበቅ ሲባል ከ40 በታች እንዲሆን ተደርጎ የተዋቀረ ነው።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2