ዛሬ ግንቦት 20 ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia | የደርግ ሥርዓት ማክተሚያ ተደርጎ ለዓመታት በአገር አቀፍ ደረጃ ሲከበር የቆየው የግንቦት 20 መታሰቢያ ዕለት፣ ዘንድሮ በፌዴራል እና በክልል ደረጃ የተለያየ መልክ ይዞ ውሏል።

​በፌዴራል መንግሥት ደረጃ በ2016 ዓ.ም በወጣው አዲስ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበር አዋጅ መሠረት፣ ቀኑ ከብሔራዊ በዓልነት ተሰርዟል።

በዚህም ምክንያት በዛሬው ዕለት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግሥትና የግል መሥሪያ ቤቶች፣ እንዲሁም የትምህርት ተቋማት መደበኛ ሥራቸውንና አገልግሎታቸውን ሳያቋርጡ ቀጥለዋል።

​በሌላ በኩል በትግራይ ክልል ቀኑን አስመልክቶ የተለየ አቀራረብ ታይቷል። በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች ተዘግተው የዋሉ ሲሆን፣ የክልሉ መገናኛ ብዙኃንም ቀኑንና ታሪካዊ አንድምታውን የሚያስታውሱ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ሲያስተላልፉ ውለዋል።

​ይህ በፌዴራል እና በክልሉ መካከል የታየው የአከባበር ልዩነት፣ በአዲሱ አዋጅ እና በክልሉ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ መሆኑን መረዳት ተችሏል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#ግንቦት20 #ኢትዮጵያ #ትግራይ #የሕዝብበዓላት #ወቅታዊዜና #ቲክቫህ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2