#Ethiopia | አዲስ እይታ ቢዝነስ አማካሪ እና አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስትራቴጂካዊ የመግባቢያ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የአዲስ እይታ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክብረት አካሳ እና የአሚጎስ ሴንትራል ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ገለታው ፀጋው የፈረሙት ሲሆን በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በወቅቱም አቶ ክብረት አካሳ እንደገለጹት አዲስ እይታ ላለፉት 10 ዓመታት ዜጎችን በቢዝነስ ክህሎት በማልመድ እና የሥራ ማሽኖችን ከውጭ በማስገባት አምራች ኃይል ለመፍጠር እየሠራ ይገኛል።
ከአሚጎስ ጋር የተደረገው ይህ ስምምነትም ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው እምነታቸውን ገልጸዋል።
የአሚጎስ ሲኒየር ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኦፊሰር አቶ ነጋሲ ስዩም በበኩላቸው ተቋማቸው ላለፉት 13 ዓመታት በታማኝነትና በትጋት በመሥራት የዜጎችን የቁጠባ ባህል ማሳደጉን ጠቅሰው አብሮ የመሥራት ባህል ለስኬታቸው ምሰሶ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህ ስምምነትም ወደ ቢዝነስ ለሚገቡ ዜጎች የሚስተዋለውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳለው አብራርተዋል።
የአሚጎስ ሴንትራል ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ገለታው ፀጋው ስምምነቱ ትልቅ ስኬት መሆኑንና የጋራ ተጠቃሚነትን እንደሚያረጋግጥ ተናግረዋል።
አሚጎስ በአሁኑ ወቅት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዜጎች ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ ለማሽን ግዥና ለቢዝነስ ማስፋፊያ ያቀደውን ሰፊ ሥራ ስኬታማ ለማድረግ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካለው ከአዲስ እይታ ቢዝነስ አማካሪ ጋር መሥራቱ ተጨባጭ ውጤት እንደሚያስገኝም ገልጸዋል።
***
📢 አዲስ እይታ ቢዝነስ አማካሪ
ቢዝነስ ለመጀመር፣ ለማሳደግ ወይም አዳዲስ የቢዝነስ ሀሳቦችን ለማግኘት ታማኝ አማካሪ እየፈለጉ ነው?
የ10 ዓመታት ልምድን ያካበተው አዲስ እይታ ቢዝነስ አማካሪ ከእርስዎ ጋር ነው!
✅ የተጠኑ የቢዝነስ ሀሳቦች
✅ የቢዝነስ እቅድ ዝግጅት
✅ የገበያ አዋጭነት ጥናት
✅ የቢዝነስ ስልጠናና ምክር
✅ የማምረቻ ማሽኖች አቅርቦት
✅ የቢዝነስ ማስፋፊያና…ሌሎችም የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት አተገባበር ስልቶችን ማማከር፤
📍 አድራሻ:
ሜክሲኮ፣ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 227
📞 ስልክ: 0978212121 / 0901842121
🌐 በተለያዩ አማራጮች ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
በዚህ ፈጣን ዘመን አዲስ እይታን ሳያማክሩ ወደ ቢዝነስ እንዳይገቡ!
🎯 አዲስ እይታ ቢዝነስ አማካሪ — ህልምዎን እንተገብራለን!
#አዲስእይታ #አሚጎስ #የቁጠባናብድር #ቢዝነስ #ፋይናንስ #ኢንቨስትመንት #ሥልጠና #ማኑፋክቸሪንግ #አዲስአበባ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.