ፓልም ሪል እስቴት ለደንበኞቹ ሱቆችን ባስረከበበት ሁነት ላይ ለመቄዶንያ የባለ ሶስት መኝታ አፓርትመንት በስጦታ አበርክቷለ።

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ፓልም ሪል እስቴት “በጥራት እና በታማኝነት መልካም ሕይወትን እንገነባለን” በሚል መርህ በገርጂ አንበሳ ጋራጅ አካባቢ የገነባቸውን 126 የንግድ ሱቆች በዛሬዉ እለት ለደንበኞቹ አስረከበ።

ድርጅቱ ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ 128 አፓርትመንቶች እና 4 ፔንት ሐውሶችም ለርክክብ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቋል።

ድርጅቱ ከባሕር ወለል ጀምሮ እስከ 3ኛ ፎቅ ድረስ ለሱቆች /ለንግድ የተዘጋጁ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ለጂም እና ለስፓ አገልግሎት የተሰጠው 4ኛ ፎቅ መሆኑን እንዲሁም የመኖሪያ ክፍሎቹ የሚጀምሩት ከ5ኛ ፎቅ ሲሆን እስከ 21ኛ ፎቅ ድረስ መሆናቸዉ ነዉ የተገለፀዉ።

የተረከቡት ሱቆችና መኖሪያዎች ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ታስቦ ከግንባታው ጋር እኩል የትራንስፎርመርና የተጠባባቂ ጄኔሬተር ተከላ ስራ የተጠናቀቀላቸው ሲሆን፣ የ24 ሰዓት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትና የ200 መኪና ማቆሚያ ቤዝመንት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ድርጅቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት፣ ለመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና አረጋውያን መርጃ ማህበር 177.48 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውና ከ28.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ባለ 3 መኝታ ዘመናዊ አፓርትመንት በስጦታ አበርክቷል።

የተበረከተው አፓርትመንት 177.48 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው፣ ባለ 3 መኝታ፣ ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ያካተተ እና ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ መኖሪያ ቤት ነው፡፡

የፓልም ሪል እስቴት ጠቅላላ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አዱኛ ማዕምር በበኩላቸው፣ድርጅቱ የሚገነባው ሕንፃዎችን ብቻ ሳይሆን የደንበኞቹን እምነትና የነገ ተስፋ ጭምር መሆኑን ጠቅሰው፤ የገርጂ ፕሮጀክት የድርጅቱን የቃል ኪዳን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኘው የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አርቲስት አለማየሁ ታደሰ በበኩሉ ፣ ተቋሙ በጥራትና በተግባር የሚሰራ በመሆኑ አምባሳደር በመሆኔ ደስተኛ ነኝ ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል።

ፓልም ሪል እስቴት በአሁኑ ወቅት ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶችንም እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ የደምበል ፕሮጀክቱ ከ60% በላይ መድረሱንና የፒያሳ ሳይት 4 ቤዝመንቶችን አጠናቆ ወደ አንደኛ ፎቅ ግንባታ መሸጋገሩን ገልጿል።

በተጨማሪም በአፍሪካ ሕብረት አካባቢ (ጋማ ፕሮጀክት) በ7,800 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ፣ ከ500 በላይ አፓርትመንቶችና ከ600 በላይ የንግድ ቦታዎችን የሚይዝ ባለ 3 ታወር ግዙፍ የG+21 ሕንፃ ግንባታ በቅርቡ ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1